Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 30:30 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

30 ቆዳዬ ጠቈረ፥ ከእኔም ተለይቶ እርግፍግፍ አለ፥ አጥንቴም ከትኩሳት የተነሣ ተቃጠለ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

30 ቈዳዬ ጠቍሮ ተቀረፈ፤ ዐጥንቴም በትኵሳት ነደደ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

30 ቆዳዬ ጠቊሮ ተገለፈፈ፤ ሰውነቴም በትኩሳት ተቃጠለ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

30 ቍር​በቴ እጅግ ጠቈረ፥ አጥ​ን​ቶቼም ከት​ኩ​ሳት የተ​ነሣ ተቃ​ጠሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

30 ቁርበቴ ጠቈረ፥ ከእኔም ተለይቶ እርግፍግፍ አለ፥ አጥንቴም ከትኵሳት የተነሣ ተቃጠለች።

参见章节 复制




ኢዮብ 30:30
11 交叉引用  

መበስበስን፦ አንተ አባቴ ነህ፥ ትልንም፦ አንቺ እናቴ እኅቴም ነሽ ብያለሁ።


ሰይጣንም ከጌታ ፊት ወጣ፥ ኢዮብንም ከእግሩ መርገጫ ጀምሮ እስከ አናቱ ድረስ በክፉ ቁስል መታው።


የሌሊቱ ስቃይ እስከ አጥንቶቼ ድረስ ይዘልቃል፥ ሁለመናዬንም ስለሚበላኝ ጅማቶቼ አያርፉም።


በመከራዬ ቀን ፊትህን ከኔ አትመልስ፥ ጆሮህን ወደ እኔ አዘንብል፥ በጠራሁህ ቀን ፈጥነህ ስማኝ።


ዘመኔ እንደ ጢስ አልቃለችና፥ አጥንቶቼም እንደ ማንደጃ ተቃጥለዋልና።


በጢስ ውስጥ እንዳለ አቁማዳ ሆኛለሁና፥ ሥርዓትህን ግን አልረሳሁም።


ሜም። ከላይ እሳትን ወደ አጥንቴ ሰደደ በረታችበትም፥ ለእግሬ ወጥመድ ዘረጋ ወደ ኋላም መለሰኝ፥ አጠፋኝም ቀኑንም ሁሉ አደከመኝ።


ቤት። ሥጋዬንና ቁርበቴን አስረጀ፥ አጥንቴን ሰበረ።


ሔት። ፊታቸው ከጥቀርሻ ይልቅ ጠቁሮአል፥ በመንገድም አልታወቁም፥ ቁርበታቸው ወደ አጥንታቸው ተጣብቆአል፥ ደርቆአል፥ እንደ እንጨት ሆኖአል።


ከሚያቃጥል ከራብ ትኩሳት የተነሣ ቁርበታችን እንደ ምድጃ ጠቈረ።


እኔ ሰምቻለሁ፥ አንጀቴ ራደብኝ፥ ከድምፁ የተነሣ ከንፈሮቼ ተንቀጠቀጡ፤ መበስበስ ወደ አጥንቶቼ ውስጥ ገባ፥ በውስጤም ተንቀጠቀጥሁ፥ በአስጨነቁን ሕዝብ ላይ እስኪመጣ ድረስ፥ የመከራን ቀን ዝም ብዬ እጠብቃለሁ።


跟着我们:

广告


广告