Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 23:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 እርሱ ግን የሚተካከለው የለውም፥ ማንስ ውሳኔውን ያስቀይረዋል? የወደደውንም ያደርጋል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 “እርሱ ግን ራሱን ችሎ ብቻውን የሚኖር ነው፤ የሚቋቋመውስ ማን ነው? እርሱ የፈቀደውን ያደርጋል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 “እርሱ ራሱ ይወስናል፤ እርሱንም የሚቃወም የለም፤ እርሱ የወደደውን ሁሉ ያደርጋል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 “ስለ ፍርድ የሚ​ከ​ራ​ከር ማን ነው? እርሱ የወ​ደ​ደ​ውን ያደ​ር​ጋ​ልና።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 እርሱ ግን ብቻውን ነው፥ እርሱንስ የሚመስለው ማን ነው? ነፍሱም የወደደችውን ያደርጋል።

参见章节 复制




ኢዮብ 23:13
21 交叉引用  

እነዚህንም ነገሮች በልብህ ውስጥ ሰወርህ፥ ይህ ሁሉ በአሳብህ እንዳለ አውቃለሁ።


ከዚህም በላይ በደለኛ እንዳልሆንሁ፥ ከእጅህም የሚያድን እንደሌለ አንተ ታውቃለህ።


እርሱ ቢያልፍ፥ ቢዘጋም፥ ጉባኤንም ቢሰበስብ፥ የሚከለክለው ማን ነው?


እነሆ፥ ካፈረሰ፥ የፈረሰው ተመልሶ አይሠራም፥ በሰውም ላይ ከዘጋ፥ ሊከፈት አይችልም።


ከተናገራቸው ትእዛዛት አልኮበለልኩም፥ የአፉን ቃል በልቤ ደብቄአለሁ።


በእኔ ላይ የወሰነውን ይፈጽማል፥ እንደዚህ ያሉ ብዙ ብያኔዎች እንዳሉት።


ሕዝብንም ሆነ ሰውን በተመለከተ፥ ዝም ቢል የሚፈርድ ማን ነው? ፊቱንስ ቢሰውር የሚያየው ማን ነው?


አምላካችንስ በላይ በሰማይ ነው፥ የፈቀደውን ሁሉ አደረገ።


በሰማይና በምድር በባሕርና በጥልቆች ሁሉ፥ ጌታ የወደደውን ሁሉ አደረገ።


በሰው ልብ ብዙ አሳብ አለ፥ የጌታ ምክር ግን እርሱ ይጸናል።


ጠማማ ሊቀና አይችልም፥ የጐደለም ሊቈጠር ዘንድ አይችልም።


እግዚአብሔር የሚያደርገው ሁሉ ለዘለዓለም እንደሚኖር አወቅሁ፥ ምንም የሚጨመርበት ወይም የሚቀነስለት የለም፥ እግዚአብሔርም ሰዎች ይፈሩ ዘንድ አደረገ።


በመጀመሪያ መጨረሻውን፥ ከጥንትም ያልተደረገውን እነግራለሁ፤ “ምክሬ ትጸናለች ፈቃዴንም ሁሉ እፈጽማለሁ” እላለሁ።


ከምሥራቅ ነጣቂ ወፍን፥ ከሩቅም አገር ምክሬን የሚያደርገውን ሰው እጠራለሁ። ተናግሬአለሁ እፈጽምማለሁ፤ አስቤአለሁ አደርግማለሁ።


እንግዲህ “ታዲያ ለምን እስከ አሁን ስህተት ይፈልጋል? ፈቃዱን ሊቃወም ማን ይችላል?” ብለህ ትጠይቀኝ ይሆናል።


መልካም ስጦታ ሁሉ፥ ፍጹምም በረከት ሁሉ፥ እንደ ጥላ መዘዋወር ወይም መለዋወጥ ከሌለበት ከላይ ከብርሃናት አባት ይወርዳሉ።


跟着我们:

广告


广告