Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 22:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 ወደ እርሱም ትጸልያለህ፥ እርሱም ይሰማሃል፥ ስእለትህንም ትሰጣለህ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 ወደ እርሱ ትጸልያለህ፤ እርሱም ይሰማሃል፤ አንተም ስእለትህን ትሰጣለህ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 ወደ እርሱም በምትጸልይበት ጊዜ የለመንከውን ሁሉ ስለሚፈጽምልህ፥ ስለትህን ትከፍላለህ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 ወደ እር​ሱም ትጸ​ል​ያ​ለህ፥ እር​ሱም ይሰ​ማ​ሃል፤ ስእ​ለ​ት​ህ​ንም ይሰ​ጠ​ሃል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 ወደ እርሱም ትጸልያለህ፥ እርሱም ይሰማሃል፥ ስእለትህንም ትሰጣለህ።

参见章节 复制




ኢዮብ 22:27
22 交叉引用  

ከዚህ በኋላ ኢዮአካዝ ወደ እግዚአብሔር ጸለየ፤ እግዚአብሔርም የሶርያ ንጉሥ በእስራኤላውያን ላይ የፈጸመባቸው ግፍ እጅግ ከባድ መሆኑን ተመልክቶ የኢዮአካዝን ጸሎት ሰማ።


ያቤጽም፦ “እባክህ፥ መባረክን ባርከኝ፥ አገሬንም አስፋው፤ እጅህም ከእኔ ጋር ይሁን፤ እንዳይጎዳኝም ከክፋት ጠብቀኝ” ብሎ የእስራኤልን አምላክ ጠራ፤ እግዚአብሔርም የለመነውን ሰጠው።


ወደ እርሱም ጸለየ፤ እርሱም ተለመነው፥ ጸሎቱንም ሰማው፥ ወደ መንግሥቱም ወደ ኢየሩሳሌም መለሰው፤ ምናሴም እርሱ ጌታ አምላክ እንደሆነ አወቀ።


“አንተ ልብህን ቅን ብታደርግ፥ እጆችህን ወደ እርሱ ትዘረጋለህ፥ በእጅህ በደል ቢኖር አርቀው፥ በድንኳንህም ኃጢአት አይኑር፥


ሁሉንስ በሚችል አምላክ ደስ ይለዋልን? እግዚአብሔርንስ ሁልጊዜ ይጠራልን?


ወደ እግዚአብሔር ይጸልያል፥ እርሱም ይሰማዋል፥ ፊቱንም በደስታ ያሳየዋል፥ ለሰውም የጽድቁን ዋጋ ይመልስለታል።


ንጹሕና ቅን ብትሆን፥ በእውነት እርሱ አንተን ነቅቶ ይጠብቅሃል፥ የጽድቅህንም መኖሪያ ያረጋግጥልሃል።


ሃሌ ሉያ! ጌታ የልመናዬን ድምፅ ሰምቶአልና ወደድሁት።


በሕዝቡ ሁሉ ፊት፥ እነሆ ስእለቴን ለጌታ እፈጽማለሁ።


በእግዚአብሔር ታመንሁ፥ አልፈራም፥ ሰው ምን ያደርገኛል?


በድንኳንህ ለዘለዓለም እኖራለሁ፥ በክንፎችህም ጥላ እጋረዳለሁ፥


ይጠራኛል እመልስለትማለሁ፥ በመከራውም ጊዜ ከእርሱ ጋራ እሆናለሁ፥ አድነዋለሁ አከብረውማለሁ።


ተስለህ ካለመፈጸም ባትሳል ይሻላል።


የዚያን ጊዜ ትጠራለህ ጌታም ይሰማሃል፤ ትጮኻለህ እርሱም፦ እነሆኝ ይላል። ከመካከልህ ቀንበርን ብታርቅ፥ በጣትህም መጠቆም ብትተው፥ ባታንጐራጉርም፥


እናንተም ትጠሩኛለችሁ፤ ሄዳችሁም ወደ እኔ ትጸልያላችሁ፤ እኔም እሰማችኋለሁ።


ከንቱነትንና ሐሰትን የሚጠብቁ ምሕረታቸውን ትተዋል።


ለእግዚአብሔር ለጌታ ስእለት በተሳልህ ጊዜ እግዚአብሔር ጌታ ከአንተ ፈጽሞ ይሻዋልና፥ ኃጢአትም ይሆንብሃልና ከመክፈል አታዘገይ።


跟着我们:

广告


广告