Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 22:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

2 “በውኑ ሰው እግዚአብሔርን ይጠቅመዋልን? ይልቁንም ጥበበኛ ሰው ራሱን ይጠቅማል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

2 “ሰው እግዚአብሔርን ሊጠቅም ይችላልን? ጠቢብ እንኳ ቢሆን ምን ይጠቅመዋል?

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

2 “ሰው እግዚአብሔርን ሊጠቅም ይችላልን? ሌላው ቀርቶ ጠቢብ እንኳ ቢሆን ጥቅሙ ለራሱ እንጂ ለእግዚአብሔር አይሆንም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

2 “በውኑ ማስ​ተ​ዋ​ል​ንና ዕው​ቀ​ትን የሚ​ያ​ስ​ተ​ምር፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር አይ​ደ​ለ​ምን?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

2 በውኑ ሰው እግዚአብሔርን ይጠቅመዋልን? በእውነት ጥበበኛ ሰው ራሱን ይጠቅማል።

参见章节 复制




ኢዮብ 22:2
15 交叉引用  

እናመልከውስ ዘንድ ሁሉን የሚችል አምላክ ማን ነው? ወይስ ወደ እርሱ ብንጸልይ ምን ይጠቅመናል?” ይላሉ።


ቴማናዊውም ኤልፋዝ መለሰ፤ እንዲህም አለ፦


ጻድቅ መሆንህስ ሁሉን የሚችለውን አምላክ ደስ ያሰኘዋልን? መንገድህን ማቅናትህስ ይጠቅመዋልን?


ሰው ምንድነው ታከብረው ዘንድ፥ ልብህንስ ትጥልበት ዘንድ፥


ጌታን፦ “አንተ ጌታዬ ነህ አልሁ”፥ ከአንተ በቀር በጎነት የለኝም።


ጠቢብ ብትሆን ለራስህ ጠቢብ ትሆናለህ፥ ፌዘኛም ብትሆን ፌዘኛነትህን ለብቻህ ትሸከማለህ። (የሚቀጥለው ከግሪክ የተጨመረ ነው።) ልጄ ለራስህ አዋቂ ብትሆን ለባልንጀራህም አዋቂ ትሆናለህ፥ ለራስህ ክፉ ብትሆን ግን ክፋትን ለብቻህ ትሸከማለህ። ሐሰትን የሚያዘጋጅ ሰው ነፋሳትን እንደሚገዛ ነው፥ የሚበርር ወፍንም እንደሚከተል ይመስላል። የወይኑ ቦታ መንገዱን ረስቷልና፥ የሚሠማራባትን መንገድ እንዲስት አድርጓልና፥ ወደ ምድረ በዳ ይሄዳል፥ ለጥም ወደ ተሠራች አገር ይሄዳል፥ የማያፈራ የማይጠቅም ገንዘብንም በእጁ ይሰበስባል።


ቀኝ ዐይንህ ብታሰናክልህ ከአንተ አውጥተህ ጣላት፤ ሰውነትህ በሙሉ ወደ ገሃነም ከሚጣል ይልቅ ከሰውነትህ አንዱ ክፍል ቢጠፋ ይሻልሃልና።


እንዲሁ እናንተ ደግሞ የታዘዛችሁትን ሁሉ ባደረጋችሁ ጊዜ ‘የማንጠቅም አገልጋዮች ነን፤ ልናደርገው የሚገባንን አድርገናል፤’ በሉ።”


እርሱም ሕይወትንና እስትንፋስን ሁሉንም ለሁሉ ይሰጣልና፥ አንዳች እንደሚጎድለው በሰው እጅ አይገለገልም።


መልካም እንዲሆንልህ ዛሬ ለአንተ የማዝዘውን የጌታን ትእዛዝና ሥርዓት እንድትጠብቅ ነው።


跟着我们:

广告


广告