ኢዮብ 19:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)4 በእውነትም የሳትሁ እንደሆነ፥ ስሕተቴ ከእኔ ጋር ትኖራለች። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም4 በእውነት ተሳስቼ ከሆነ፣ ስሕተቱ የራሴ ጕዳይ ነው። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም4 በእርግጥ ተሳስቼ ከሆነ፥ ስሕተቱ የሚጐዳው ራሴን ብቻ ነው። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)4 በእውነት እኔ ከበደልሁ፤ ስሕተቴ ከእኔ ጋር ትኖራለች። የማላውቀውንም ነገር ተናገርሁ፤ ነገሬም ስንፍና ነው እንጂ በየጊዜው አይደለም። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)4 በእውነትም የሳትሁ እንደ ሆነ፥ ስሕተቴ ከእኔ ጋር ትኖራለች። 参见章节 |
ጠቢብ ብትሆን ለራስህ ጠቢብ ትሆናለህ፥ ፌዘኛም ብትሆን ፌዘኛነትህን ለብቻህ ትሸከማለህ። (የሚቀጥለው ከግሪክ የተጨመረ ነው።) ልጄ ለራስህ አዋቂ ብትሆን ለባልንጀራህም አዋቂ ትሆናለህ፥ ለራስህ ክፉ ብትሆን ግን ክፋትን ለብቻህ ትሸከማለህ። ሐሰትን የሚያዘጋጅ ሰው ነፋሳትን እንደሚገዛ ነው፥ የሚበርር ወፍንም እንደሚከተል ይመስላል። የወይኑ ቦታ መንገዱን ረስቷልና፥ የሚሠማራባትን መንገድ እንዲስት አድርጓልና፥ ወደ ምድረ በዳ ይሄዳል፥ ለጥም ወደ ተሠራች አገር ይሄዳል፥ የማያፈራ የማይጠቅም ገንዘብንም በእጁ ይሰበስባል።