Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 16:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 እኔ ደግሞ እንደ እናንተ እናገር ዘንድ ይቻለኝ ነበር፥ ነፍሳችሁ በነፍሴ ፋንታ ቢሆን ኖሮ፥ እኔ በእናንተ ላይ ቃል ማሳካት፥ ራሴንም በእናንተ ላይ መነቅነቅ በተቻለኝ ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 እናንተ በእኔ ስፍራ ብትሆኑ ኖሮ፣ እኔም እንደ እናንተ መናገር እችል ነበር፤ ቃላት አሳክቼ በመናገር፣ በእናንተ ላይ ራሴን መነቅነቅ በቻልሁ ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 እናንተ በእኔ ቦታ ሆናችሁ እኔ በእናንተ ቦታ ብሆን ኖሮ በንቀት ራሴን እየነቀነቅሁ አሁን እናንተ የምትሉትን ሁሉ በእናንተ ላይ አሳምሬ መናገር በቻልኩ ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 እኔ ደግሞ እና​ንተ እን​ደ​ም​ት​ና​ገሩ እና​ገር ነበር፤ ነፍ​ሳ​ችሁ በነ​ፍሴ ፋንታ ብት​ሆን ኖሮ፥

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 እኔ ደግሞ እንደ እናንተ እናገር ዘንድ ይቻለኝ ነበር፥ ነፍሳችሁ በነፍሴ ፋንታ ቢሆን ኖሮ፥ እኔ በእናንተ ላይ ቃል ማሳካት፥ ራሴንም በእናንተ ላይ መነቅነቅ በተቻለኝ ነበር።

参见章节 复制




ኢዮብ 16:4
21 交叉引用  

ስለ እርሱ እግዚአብሔር የተናገረው ቃል ይህ ነው፦ የጽዮን ድንግል ትንቅሃለች፤ ታፌዝብሃለች፤ አንተ እየሸሸህ ሳለህ፥ የኢየሩሳሌም ልጃገረዶች ከኋላህ ሆነው ራሳቸውን ይነቀንቁብሃል።


“በውኑ ነገር ለሚያበዛ መልስ መስጠት አይገባምን? ወይስ ተናጋሪ ሰው እንደ ጻድቅ ይቈጠራልን?


በአፌም ነገር ባበረታኋችሁ ነበር፥ የከንፈሬን ማጽናናት ባልከለከልሁም ነበር።”


ስለዚህ ኢዮብ ከንቱ ንግግርን ከአፉ ያወጣል፥ ያለ እውቀትም ቃሉን ያበዛል።”


“ቸርነትን ለወዳጁ የሚነፍግ፥ ሁሉን ቻይ አምላክን መፍራት የተወ ነው።


እኔም በእነርሱ ዘንድ መሳለቂያ ሆንሁ፥ ሲያዩኝ ራሳቸውን ይነቀንቃሉ።


እኔ ግን ትል ነኝ ሰውም አይደለሁም፥ የሰው ማላገጫ በሕዝብም ዘንድ የተናቅሁ ነኝ።


የሚያዩኝ ሁሉ ያፌዙበኛል፥ ራሳቸውን እየነቀነቁ በከንፈሮቻቸው እንዲህ ይሳለቃሉ፦


ለጎረቤቶቻችን ስድብ፥ በዙሪያችንም ላሉ መሣቂያና መዘበቻ አደረግኸን።


በቃል ብዛት ውስጥ መተላለፍ ሳይኖር አይቀርም፥ ከንፈሩን የሚገታ ግን አስተዋይ ነው።


ሰነፍ ቃሉን ያበዛል፥ ሰው ግን የሚሆነውን አያውቅም፥ ከእርሱስ በኋላ የሚሆነውን ማን ይነግረዋል?


ጌታ ስለ እርሱ የተናገረው ቃል ይህ ነው፦ ‘ድንግሊቱ የጽዮን ልጅ ቀላል አድርጋሃለች፥ በንቀትም ስቃብሃለች፤ የኢየሩሳሌም ልጅ ስትሸሽ ራስዋን ነቅንቃብሃለች።


ምድራቸውን ለመሣቀቂያና ለዘለዓለም ማፍዋጫ አድርገዋል፤ የሚያልፍባት ሁሉ ይደነቃል፥ ራሱንም ይነቀንቃል።


ለአንተ እስራኤል መሳቂያ አልነበረምን? ወይስ ስለ እርሱ በተናገርህ ቊጥር ራስህን የምትነቀንቀው በሌቦች መካከል ተገኝቶአልን?።


ሳምኬት። መንገድ አላፊዎች ሁሉ እጃቸውን ያጨበጭቡብሻልና፦ በውኑ የውበት ፍጻሜና የምድር ሁሉ ደስታ የሚሉአት ከተማ ይህች ናትን? እያሉ፥ በኢየሩሳሌም ሴት ልጅ ላይ ያፍዋጫሉ፥ ራሳቸውንም ያነቃንቃሉ።


ስጋት ሳይኖርባት የተቀመጠች ደስተኛይቱ ከተማ ይህች ናት፥ በልብዋም፦ “እኔ ነኝ፥ ከእኔም በቀር ሌላ የለም” ያለች፥ እንዴት አራዊት የሚመሰጉባት ባድማ ሆነች! በእርሷ በኩል የሚያልፈው ሁሉ እጁን እያወዛወዘ ያፏጫል።


እንግዲህ ሰዎች ሊያደርጉላችሁ የምትፈልጉትን ሁሉ እናንተ ደግሞ እንዲሁ አድርጉላቸው፤ ሕግና ነቢያትም ይህ ነውና።


ደስ ከሚላቸው ጋር ደስ ይበላችሁ፤ ከሚያለቅሱ ጋር አልቅሱ።


አንድም አካል ቢሠቃይ የአካል ክፍሎች ሁሉ ከእርሱ ጋር ይሠቃያሉ፤ አንድ አካልም ቢከበር የአካል ክፍሎች ሁሉ ከእርሱ ጋር ደስ ይላቸዋል።


跟着我们:

广告


广告