Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 12:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 የቀማኞች ድንኳን በደኅንነት ይኖራል፥ እግዚአብሔርንም የሚያስቈጡ ተዝናንተው ተቀምጠዋል፥ እግዚአብሔር ሁሉን በእጃቸው አምጥቶላቸዋል።”

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 የቀማኞች ድንኳን አይታወክም፤ አምላካቸውን በእጃቸው ይዘው እየዞሩም፣ እግዚአብሔርንም እያስቈጡ በሰላም ይኖራሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 ኀይላቸውን እንደ አምላክ አድርገው የሚቈጥሩ ሌቦችና እግዚአብሔርን የካዱ ሰዎች እንኳ በሰላም ይኖራሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን የሚ​ያ​ስ​ቈ​ጡ​ትን ሰዎች፥ እርሱ የሚ​መ​ረ​ም​ራ​ቸው አይ​ደ​ለ​ምን?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 የቀማኞች ድንኳን በደኅንነት ይኖራል፥ እግዚአብሔርንም የሚያስቈጡ ተዘልለው ተቀምጠዋል፥ እግዚአብሔር ሁሉን በእጃቸው አምጥቶላቸዋል።

参见章节 复制




ኢዮብ 12:6
17 交叉引用  

ተደላድሎ የተቀመጠ ሰው መከራን ይንቃል፥ እግሩን ያዳለጠውንም ለመገፍተር ተዘጋጅቶአል።


“አሁን ግን እንስሶችን ጠይቅ፥ ያስተምሩህማል፥ የሰማይንም ወፎች ጠይቅ፥ ይነግሩህማል።


ቁጣህን በእግዚአብሔር ላይ እስከ ማንሣት ደርሰህ፥ እነኚህንም ቃላት ከአፍህ እስከ ማውጣት ደርሰህ።


“ነገር ግን ቤታቸውን በመልካም ነገር ሞልቶት ነበር፥ የክፉ ሰው ምክር ከእኔ ዘንድ የራቀች ናት።


እግዚአብሔር በደኅና አኑሮአቸዋል፥ በዚያም ይታመናሉ፥ ዐይኖቹ ግን መንገዳቸውን ይመለከታሉ።


ምድር በኃጥአን እጅ ተሰጥታለች፥ የፈራጆችዋን ፊት ሸፍኖአል፥ ይህንን ያደረገው እርሱ ካልሆነ ሌላ ማን ነው?”


አቤቱ፥ ከሰዎች፥ እድል ፈንታቸው በሕይወታቸው ከሆነች ከዚህ ዓለም ሰዎች በእጅህ አድነኝ፥ ከሰወርኸው መዝገብህ ሆዳቸውን አጠገብህ፥ ልጆቻቸው ተትረፍርፎላቸዋል የተረፋቸውንም ለሕፃናቶቻቸው ያተርፋሉ።


የዳዊት መዝሙር። በክፉዎች ላይ አትቅና፥ ዓመፃንም በሚያደርጉ ላይ አትቅና፥


ክፉን በጭቆና ከፍ ከፍ ብሎ እንደ ሊባኖስ ዝግባም ለምልሞ አየሁት።


የክፉዎችን ሰላም አይቼ በዓመፀኞች ቀንቼ ነበርና።


የማያስተውል ሰው አያውቅም። አላዋቂ አይረዳውም።


አቤቱ! ከአንተ ጋር በተምዋገትሁ ጊዜ አንተ ጻድቅ ነህ፤ ነገር ግን ከአንተ ጋር ስለ ፍርድ ልናገር። የኃጢአተኞች መንገድ ስለምን ይቃናል? በደልንስ ለሚበድሉ ሁሉ ስለምን ደኅንነት ይሆናል?


ወፍ እንደሞላበት የወፍ ቀፎ፥ እንዲሁ ቤቶቻቸው በሽንገላ ተሞልቶአል፤ ስለዚህም ከብረዋል ባለ ጠጎችም ሆነዋል።


ወፍረዋል ሰብተዋልም፥ ክፋታቸውንም ያለ ልክ አብዝተዋል፤ የድሀ አደጎች ነገር መልካም እንዲሆንላቸው አልተምዋገቱላቸውም፥ የችግርተኞችንም ፍርድ አልፈረዱላቸውም።


የዚያን ጊዜም እንደ ነፋስ ጠራርገው ይሄዳሉ፤ ኃይላቸውን አምላካቸው ያደረጉ በደለኞች ናቸው።


跟着我们:

广告


广告