Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢዮብ 12:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 ብርሃንም በሌለበት ጨለማ ይርመሰመሳሉ፥ እንደ ሰካራም ያቅበዘብዛቸዋል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 ብርሃን በሌለበት ጨለማ በዳበሳ ይሄዳሉ፤ እንደ ሰካራምም ይንገዳገዳሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 ብርሃን አጥተው በጨለማ እንዲደናበሩና እንደ ሰከረም ሰው እንዲንገዳገዱ ያደርጋቸዋል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 ብር​ሃ​ንም ሳይ​ኖር በጨ​ለማ ይር​መ​ሰ​መ​ሳሉ፤ እንደ ሰካ​ራ​ምም ይፍ​ገ​መ​ገ​ማሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 ብርሃንም ሳይኖር በጨለማ ይርመሰመሳሉ፥ እንደ ሰካራም ይቅበዘበዛሉ።

参见章节 复制




ኢዮብ 12:25
10 交叉引用  

በቤቱ ደጃፍ የነበሩትንም ሰዎች ከታናሻቸው ጀምሮ እስከ ታላቃቸው ድረስ አሳወሩአቸው፥ ሰዎቹም ደጃፉን ለማግኘት ሲፈልጉ ደከሙ።


ብርሃን በድንኳኑ ውስጥ ይጨልማል፥ መብራቱም በላዩ ይጠፋል።


በቀን ጨለማን ያገኛሉ፥ በቀትርም ጊዜ በሌሊት እንዳሉ ይርመሰመሳሉ።


ደነገጡ እንደ ስካርም ተንገደገዱ፥ ጥበባቸውም ሁሉ ተዋጠች።


ጌታ ግራ የመጋባት መንፈስ በውስጥዋ አፍሶባታል፤ ሰካራም በትፋቱ ዙሪያ እንደሚንገዳገድ እንዲሁ ግብጽን በሥራዋ ሁሉ እንድትንገዳገድ አደረጓት።


ምድር እንደ ሰካራም ትንገዳገዳለች፥ እንደ ዳስም ትወዛወዛለች፤ መተላለፍዋ ከብዷታል፥ ትወድቃለች፥ ደግማም አትነሣም።


እንደ ዕውሮች ወደ ቅጥሩ ተርመሰመስን፥ ዐይን እንደሌላቸው ተርመሰመስን፤ በቀትር ጊዜ በድግዝግዝታ እንዳለ ሰው ተሰናከልን፥ እንደ ሙታን በጨለማ ስፍራ ነን።


አሁንም፥ እነሆ፥ የጌታ እጅ በአንተ ላይ ናት፤ ዕውርም ትሆናለህ እስከ ጊዜውም ፀሐይን አታይም፤” አለው። ያን ጊዜም ጭጋግና ጨለማ ወደቀበት፤ በእጁም የሚመራውን እየዞረ ፈለገ።


በእኩለ ቀን ዕውር በዳበሳ እንደሚሄደው ትሄዳለህ። የምታደርገው ሁሉ አይሳካልህም። ዘወትር ትጨቆናለህ፤ ያለማቋረጥም ትመዘበራለህም፤ የሚታደግህ አይኖርም።


ወንድሙን የሚጠላ ግን በጨለማ ይኖራል፥ በጨለማም ይመላለሳል፥ ጨለማው ዐይኖቹን ስላሳወረው ወዴት እንደሚሄድ አያውቅም።


跟着我们:

广告


广告