Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 52:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 የሴዴቅያስንም ዐይኖች አወጣ፤ የባቢሎንም ንጉሥ በሰንሰለት አሰረው ወደ ባቢሎንም ወሰደው፥ እስኪሞትም ድረስ በእስር ቤት አኖረው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 የሴዴቅያስንም ዐይኖች አወጣ፤ በናስ ሰንሰለትም አሰረው። የባቢሎንም ንጉሥ ወደ ባቢሎን ወሰደው፤ በዚያም እስከ ዕለተ ሞቱ በእስር ቤት አቈየው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ከዚያም በኋላ የሴዴቅያስን ዐይኖች አውጥቶ በእግር ብረት በማሰር ወደ ባቢሎን ወሰደው፤ እስከ ሞተበትም ጊዜ ድረስ በባቢሎን እስረኛ አደረገው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 የሴ​ዴ​ቅ​ያ​ስ​ንም ዐይ​ኖች አወጣ፤ የባ​ቢ​ሎ​ንም ንጉሥ በሰ​ን​ሰ​ለት አሰ​ረው፤ ወደ ባቢ​ሎ​ንም ወሰ​ደው፤ እስ​ኪ​ሞ​ትም ድረስ በግ​ዞት ቤት አኖ​ረው።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 የሴዴቅያስንም ዓይኖች አወጣ፥ የባቢሎንም ንጉሥ በሰንሰለት አሰረው ወደ ባቢሎንም ወሰደው፥ እስኪሞትም ድረስ በግዞት ቤት አኖረው።

参见章节 复制




ኤርምያስ 52:11
7 交叉引用  

ከዚህ በኋላ፥ ይላል ጌታ፥ የይሁዳን ንጉሥ ሴዴቅያስን፥ ከቸነፈርና ከሰይፍ ከራብም በዚህችም ከተማ የቀሩትን፥ አገልጋዮቹንና ሕዝቡን በባቢሎን ንጉሥ በናቡከደነፆር እጅ በጠላቶቻቸውና ነፍሳቸውንም በሚሹት እጅ አሳልፌ እሰጣቸዋለሁ፤ እርሱም በሰይፍ ስለት ይመታቸዋል፤ አያዝንላቸውም፥ አይራራላቸውም፥ አይምራቸውም።’


የሴዴቅያስንም ዐይን አወጣ፥ ወደ ባቢሎንም ለመውሰድ በሰንሰለት አሰረው።


ዋው። ማደሪያውን እንደ አትክልት ነቀለ፥ የበዓሉን ስፍራ አጠፋ፥ እግዚአብሔር በጽዮን ዓመት በዓሉንና ሰንበቱን አስረሳ፥ በቁጣውም መዓት ንጉሡንና ካህኑን አቃለለ።


መረቤንም በእርሱ ላይ እዘረጋለሁ፥ በወጥመዴም ይያዛል፥ ወደ ከለዳውያን ምድር ወደ ባቢሎን አመጣዋለሁ፥ ሆኖም አያያትም በዚያም ይሞታል።


እኔ ሕያው ነኝና ይላል ጌታ እግዚአብሔር፥ መሐላውን የናቀበት፥ ከእርሱ ጋር የነበረውን ቃል ኪዳኑን ያፈረሰበት፥ ያነገሠው ንጉሥ በሚኖርበት ስፍራ በባቢሎን መካከል በእርግጥ ይሞታል።


መሣሪያ፥ ሠረገላና መንኰራኵር ይዘው፥ ብዙ ሕዝብ ሆነው በአንቺ ላይ ይመጣሉ፤ ጋሻና አላባሽ ጋሻ ራስ ቁርም ይዘው በዙሪያሽ ይዘጋጁብሻል፥ ፍርድንም እሰጣቸዋለሁ፥ እንደ ፍርዳቸውም ይፈርዱብሻል።


跟着我们:

广告


广告