Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 51:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 ከዳር እስከ ዳር ድረስ ከተማው እንደ ተያዘች ለባቢሎን ንጉሥ ለመንገር አንደኛው ሯጭ ሌላውን ሯጭ አንዱም መልእክተኛ ሌላውን መልእክተኛ ለመገናኘት ይሮጣል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 ከተማዪቱ ሙሉ በሙሉ መያዟን፣ ለባቢሎን ንጉሥ ለመንገር፣ አንዱ ወሬኛ ሌላውን ወሬኛ፣ አንዱ መልእክተኛ ሌላውን መልእክተኛ ወዲያው ወዲያው ይከተላል፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 የእርሱ ከተማ ከዳር እስከ ዳር የተያዘች መሆንዋን ለባቢሎን ንጉሥ ለመንገር አንዱ ሩዋጭ ለሌላው ሩዋጭ፥ አንዱ መልእክተኛ ለሌላው መልእክተኛ መልእክቱን ለማስተላለፍ ይሯሯጣሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 ለባ​ቢ​ሎን ንጉሥ ይነ​ግር ዘንድ ሯጩ ሯጩን ለመ​ገ​ና​ኘት፤ መል​እ​ክ​ተ​ኛ​ውም መል​እ​ክ​ተ​ኛ​ውን ለመ​ገ​ና​ኘት ይሮ​ጣል፤ ከተ​ማዋ ከዳር እስከ ዳር ተይ​ዛ​ለ​ችና፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31-32 ከዳር እስከ ዳር ድረስ ከተማው እንደ ተያዘች መልካዎችዋም እንደ ተያዙ፥ ቅጥርዋም በእሳት እንደ ተቃጠለ፥ ሰልፈኞችም እንደ ደነገጡ ለባቢሎን ንጉሥ ይነግር ዘንድ ወሬኛው ወሬኛውን መልእክተኛውም መልእክተኛውን ሊገናኝ ይሮጣል።

参见章节 复制




ኤርምያስ 51:31
16 交叉引用  

እንደ ንጉሡም ትእዛዝ መልክተኞቹ እንዲህ የሚለውን የንጉሡንና የሹማምንቱን ደብዳቤ ይዘው ወደ እስራኤልና ወደ ይሁዳ ሁሉ ሄዱ እንዲህም አሉ፦ “የእስራኤል ልጆች ሆይ! ጌታ ከአሦር ነገሥታት እጅ ወዳመለጠ የእናንተ ወደ ሆኑት ትሩፋን እንዲመለስ ወደ አብርሃምና ወደ ይስሐቅ ወደ እስራኤልም አምላክ ተመለሱ።


“ቀኖቼ ከሚሮጥ ሰው ይልቅ ይፈጥናሉ፥ ይሸሻሉ፥ መልካምንም አያዩም።


መከራ በመከራ ላይ ተጠርቶአል፤ ምድሪቱም ሁሉ ጠፍታለችና፤ በድንገትም ድንኳኔ በዐይን ቅጽበትም መጋረጃዎቼ ጠፉ።


በአሕዛብ መካከል ተናገሩ አውጁም፥ ዓላማውንም አንሡ፤ አውጁ፥ ሳትደብቁም እንዲህ በሉ፦ ባቢሎን ተያዘች፥ ቤል አፈረ፥ ሜሮዳክ ተሰባበረ፤ ምስሎችዋ አፈሩ፥ ጣዖታትዋ ተሰባበሩ።


ባቢሎን ሆይ! አጥምጄብሻለሁ አንቺም ሳታውቂ ተይዘሻል፤ ከጌታ ጋር ስለ ታገልሽ ተገኝተሻል ተይዘሻልም።


የባቢሎን ንጉሥ ወሬአቸውን ሰምቶአል፥ እጆቹም ደክመዋል፥ ጣርም ይዞታል፥ ምጥ ወላድ ሴትን እንደሚይዛት ጭንቀት ይዞታል።


የወንዙም መሻገርያዎች ተይዘዋል፥ የውኃ ማቆርያዎቹም በእሳት ተቃጥለዋል ወታደሮቹም በሽብር ውስጥ ናቸው።


跟着我们:

广告


广告