ኤርምያስ 50:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)24 ባቢሎን ሆይ! አጥምጄብሻለሁ አንቺም ሳታውቂ ተይዘሻል፤ ከጌታ ጋር ስለ ታገልሽ ተገኝተሻል ተይዘሻልም። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም24 ባቢሎን ሆይ፤ ወጥመድ ዘርግቼልሻለሁ፤ አንቺም ሳታውቂ ተይዘሻል፤ እግዚአብሔርን ተገዳድረሻልና፣ ተገኘሽ፤ ተያዝሽም። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም24 ባቢሎን ሆይ! በራስሽ ላይ ባጠመድሽው ወጥመድ ሳታውቂው ተያዝሽበት፤ ተይዘሽ የተጋለጥሽውም እግዚአብሔርን ስለ ተዳፈርሽ ነው። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)24 ባቢሎን ሆይ! በመከራው ተይዘሽ ጠፋሽ፤ አንቺም ይህ እንደመጣብሽ አላወቅሽም፤ እግዚአብሔርን ተቃውመሽዋልና ተገኝተሻል፤ ተይዘሽማል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)24 ባቢሎን ሆይ፥ አጥምጄብሻለሁ አንቺም ሳታውቂ ተይዘሻል፥ ከእግዚአብሔር ጋር ስለ ተዋጋሽ ተገኝተሻል ተይዘሽማል። 参见章节 |