Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 49:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

24 ደማስቆ ደከመች ለመሸሽም ዘወር አለች መንቀጥቀጥም ያዛት፥ እንደ ወላድም ሴት ጣርና ምጥ ያዛት።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

24 ደማስቆ ተዳከመች፤ ትሸሽም ዘንድ ወደ ኋላ ተመለሰች፤ ብርክ ያዛት፣ ምጥ እንደ ያዛት ሴት፣ ጭንቅና መከራ ዋጣት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

24 የደማስቆ ሕዝብ ተዳከሙ፤ ለመሸሽ ወደ ኋላ ተመለሱ ፍርሀትም ያዛቸው፤ የምጥ ጣር እንደ ያዛትም ሴት ተጨነቁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

24 ደማ​ስቆ ደከ​መች፤ ተሸ​ብ​ራም ሸሸች፤ እን​ቅ​ጥ​ቅ​ጥም ያዛት፤ እንደ ወላ​ድም ሴት ጣርና ምጥ ያዛት።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

24 ደማስቆ ደከመች ትሸሽም ዘንድ ዘወር አለች እንቅጥቅጥም ያዛት፥ እንደ ወላድም ሴት ጣርና ምጥ ያዛት።

参见章节 复制




ኤርምያስ 49:24
13 交叉引用  

ለሴቲቱም አላት፥ “በእርግዝናሽ ወራት ጭንቅሽን እጅግ አበዛለሁ፥ በጭንቅ ትወልጃለሽ፥ ይህም ሁሉ ሆኖ ፍላጎትሽ ለባልሽ ይሆናል፥ እርሱም ገዥሽ ይሆናል።”


ሽብር ይይዛቸዋል፤ ሥቃይና ጭንቀት ይደርስባቸዋል፤ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ያምጣሉ፤ እርስ በርሳቸው በድንጋጤ ይተያያሉ፤ ፊታቸውም በፍርሀት ቀይ ይሆናል።


ጠይቁ፥ ወንድ ይወልድ እንደሆነ ተመልከቱ፤ ስለምን ሰው ሁሉ እንደ ወላድ ሴት እጁን በወገቡ ላይ አድርጎ ፊቱም ሁሉ ገርጥቶ አየሁ?


እንደታመመች የበኩርዋንም እንደምትወልድ ሴት የጭንቀት ድምፅ ሰምቻለሁና፤ የጽዮን ሴት ልጅ ድምፅ በድካም ታቃስታለች፥ እጆችዋንም በመዘርጋት፦ “በነፍሰ ገዳዮች ፊት ነፍሴ ዝላለችና ወዮልኝ!” አለች።


ከተሞቹ ተይዘዋል፥ አምባዎቹም ተወስደዋል፥ በዚያም ቀን የሞዓብ ኃያላን ልብ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ልብ ሆኖአል።


እነሆ፥ እንደ ንስር ወጥቶ ይበራል ክንፉንም በባሶራ ላይ ይዘረጋል፥ በዚያም ቀን የኤዶምያስ ኃያላን ልብ ምጥ እንደ ያዛት ሴት ልብ ይሆናል።”


ድንኳኖቻቸውንና መንጋቸውን፥ መጋረጃዎቻቸውንና ዕቃዎቻቸውን ሁሉ ይወስዳሉ፤ ግመሎቻቸውንም ለራሳቸው እየነዱ ይወስዳሉ፥ እነርሱም፦ በዙሪያቸው ሁሉ ሽብር አለ፥ እያሉ ለእነርሱ ይጮኻሉ።


በጠላቶቻቸውና ነፍሳቸውን በሚሹአት ፊት ኤላምን አስደነግጣለሁ፤ በእነርሱም ላይ ጽኑ ቁጣዬ የሆነውን ክፉ ነገር አመጣባቸዋለሁ፥ ይላል ጌታ፤ እስካጠፋቸውም ድረስ በኋላቸው ሰይፍ እልክባቸዋለሁ፤


የባቢሎን ንጉሥ ወሬአቸውን ሰምቶአል፥ እጆቹም ደክመዋል፥ ጣርም ይዞታል፥ ምጥ ወላድ ሴትን እንደሚይዛት ጭንቀት ይዞታል።


ወሬውን ሰምተናል፥ እጃችን ደክማለች፤ ምጥ ወላድን ሴት እንደሚይዛት ጭንቀት ይዞናል።


ምጥ እንደ ያዛት ሴት ጭንቅ ይመጣበታል፤ በሚወለድበት ጊዜ ወደ ማኅፀን አፍ ራሱን አያቀርብምና ማስተዋል የጎደለው ልጅ ነው።


እነዚህ ሁሉ የምጥ መጀመሪያ ናቸው።


ሕዝብ በሕዝብ ላይ፥ መንግሥት በመንግሥት ላይ ይነሣል፤ በብዙ ቦታም የመሬት መንቀጥቀጥና ራብ ይሆናል፤ እነዚህ ሁሉ የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸው።


跟着我们:

广告


广告