Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 44:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ እናንተና ሚስቶቻችሁ በአፋችሁ፦ ‘ለሰማይ ንግሥት ለማጠን የመጠጥንም ቁርባን ለእርሷ ለማፍሰስ የተሳልነውን ስእለታችንን በእርግጥ እንፈጽማለን’ ብላችሁ ተናገራችሁ በእጃችሁም አደረጋችሁት፤ እንግዲህ ስእለታችሁን አጽኑ ስእለታችሁንም ፈጽሙ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 የእስራኤል አምላክ የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤ ‘እናንተና ሚስቶቻችሁ፣ “ለሰማይዋ ንግሥት ለማጠንና የመጠጥ ቍርባን ለማፍሰስ የተሳልነውን ስእለታችንን በርግጥ እንፈጽማለን” ብላችሁ የገባችሁትን ቃል በተግባር አሳይታችኋል።’ “እንግዲያውስ ወደ ኋላ አትበሉ፤ ቃል የገባችሁትን፣ ስእለታችሁንም ፈጽሙ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እን​ዲህ ይላል፦ እና​ን​ተና ሚስ​ቶ​ቻ​ችሁ በአ​ፋ​ችሁ፦ ለሰ​ማይ ንግ​ሥት እና​ጥን ዘንድ፥ የመ​ጠ​ጥ​ንም ቍር​ባን እና​ፈ​ስ​ስ​ላት ዘንድ የተ​ሳ​ል​ነ​ውን ስእ​ለ​ታ​ች​ንን በር​ግጥ እን​ፈ​ጽ​ማ​ለን አላ​ችሁ፤ በእ​ጃ​ች​ሁም አደ​ረ​ጋ​ች​ሁት፤ እን​ግ​ዲህ ስእ​ለ​ታ​ች​ሁን አጽኑ፤ ስእ​ለ​ታ​ች​ሁ​ንም ፈጽሙ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እናንተና ሚስቶቻችሁ በአፋችሁ፦ ለሰማይ ንግሥት እናጥን ዘንድ የመጠጥንም ቍርባን እናፈስስላት ዘንድ የተሳልነውን ስእለታችንን በእርግጥ እንፈጽማለን አላችሁ በእጃችሁም አደረጋችሁት፥ እንግዲህ ስእለታችሁን አጽኑ ስእለታችሁንም ፈጽሙ።

参见章节 复制




ኤርምያስ 44:25
9 交叉引用  

ክፋትን የሚሠሩ የሚደበቁበት ጨለማ ወይም የሞት ጥላ የለም።


እናንተም፦ “ከሞት ጋር ቃል ኪዳን አድርገናል፥ ከሲኦልም ጋር ተማምለናል፤ ሐሰትን መሸሸጊያችን አድርገናልና፥ በሐሰትም ተሰውረናልና የሚትረፈረፍ መቅሠፍት ባለፈ ጊዜ አይደርስብንም” ስላላችሁ፥


ይህችን ከተማ የሚወጉ ከለዳውያን መጥተው በእሳት ያነድዱአታል፥ እኔንም ለማስቈጣት በሰገነታቸው ላይ ለበዓል ካጠኑባቸው፥ ለሌሎችም አማልክት የመጠጥን ቁርባን ካፈሰሱባቸው ቤቶች ጋር ያቃጥሉአታል።


ጌታ እግዚአብሔርም እንዲህ ይላል፦ እናንተ የእስራኤል ቤት ሆይ፥ ሂዱ፥ ከዚህም በኋላ ትሰሙኝ ዘንድ ባትወድዱ ሁላችሁ ጣዖቶቻችሁን አምልኩ። ነገር ግን ከእንግዲህ ወዲህ በቁርባናችሁና በጣዖቶቻችሁ ቅዱሱን ስሜን አታረክሱም።


ንጉሡም አዘነ፤ ነገር ግን ስለ መሐላውና ከእርሱ ጋር ተቀምጠው ስለ ነበሩት ሰዎች ሲል እንዲሰጡአት አዘዘ፤


የገዛ ነውራቸውን አረፋ የሚደፍቁ እየባሰ የሚሄድ የባሕር ማዕበል ናቸው፤ ድቅድቅ ጨለማ ለዘለዓለም የተዘጋጀላቸው የሚንከራተቱ ከዋክብት ናቸው።


跟着我们:

广告


广告