ኤርምያስ 44:24 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)24 ኤርምያስም ለሕዝቡ ሁሉ ለሴቶቹም ሁሉ እንዲህ አለ፦ “በግብጽ ምድር የምትገኙ የይሁዳ ሰዎች ሁሉ የጌታን ቃል ስሙ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም24 ኤርምያስም ለሕዝቡና ለሴቶቹ ሁሉ እንዲህ አለ፤ “በግብጽ የምትኖሩ የይሁዳ ሕዝብ ሁሉ፤ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም24-25 ከይሁዳ ተሰደው በግብጽ ስለሚኖሩት ሕዝብ የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ የነገረኝን ሁሉ ለሕዝቡ ሁሉ በተለይም ለሴቶቹ እንዲህ በማለት ነገርኳቸው፦ “እናንተና ሚስቶቻችሁ ለሰማይ ንግሥት ስእለት ለመስጠት ቃል ገብታችኋል፤ ይኸውም እናንተ ለእርስዋ ዕጣን ልታጥኑላት፥ የወይን ጠጅም መባ ልታፈሱላት የገባችሁትን ቃል ኪዳን ፈጽማችኋል፤ እንግዲያውስ ቀጥሉ፤ የገባችሁትን ቃል ጠብቁ፤ መሐላችሁንም ፈጽሙ፤ 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)24 ኤርምያስም ለሕዝቡ ሁሉ፥ ለሴቶቹም ሁሉ እንዲህ አለ፥ “በግብፅ ምድር የምትኖሩ አይሁድ ሁሉ! የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)24 ኤርምያስም ለሕዝቡ ሁሉ ለሴቶቹም ሁሉ እንዲህ አለ፦ በግብጽ ምድር የምትኖሩ ይሁዳ ሁሉ፥ የእግዚአብሔርን ቃል ስሙ። 参见章节 |