ኤርምያስ 34:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)10 ወደ ቃል ኪዳኑ የገቡ አለቆች ሁሉና ሕዝቡ ሁሉ ሰምተው ማንም ሰው ወንድ ባርያውንና ሴት ባርያውን አርነት እንዲያወጣ፥ ከእንግዲህ ወዲህም ማንም እንዳይገዛቸው አደረጉ፤ እነርሱም ሰምተው አርነት አወጡአቸው። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም10 በዚህ ቃል ኪዳን የተስማሙት ባለሥልጣኖችና ሕዝቡ ሁሉ ወንድ ወይም ሴት ባሪያዎቻቸውን ነጻ ለመልቀቅና ከእንግዲህ ባሪያ አድርገው ላይገዟቸው ተስማሙ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም10 ሕዝቡና መሪዎቻቸው ሁሉ ባሪያዎቻቸውን ነጻ ለመልቀቅና እንደገና መልሰውም ባሪያዎች ላለማድረግ ተስማሙ፤ በዚህም ስምምነት መሠረት ሁሉንም ነጻ አወጡአቸው፤ 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)10 ሰው ሁሉ ወንድ ባሪያውንና ሴት ባሪያውን አርነት እንዲያወጣ፥ ከእንግዲህ ወዲህም ማንም እንዳይገዛቸው ወደ ቃል ኪዳኑ የገቡ አለቆች ሁሉና ሕዝቡ ሁሉ ሰሙ፤ አርነትም አወጡአቸው። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)10 ሰው ሁሉ ወንድ ባሪያውንና ሴት ባሪያውን አርነት እንዲያወጣ ከእንግዲህ ወዲህም ማንም እንዳይገዛቸው ወደ ቃል ኪዳኑ የገቡ አለቆች ሁሉና ሕዝቡ ሁሉ ሰሙ አርነትም አወጡአቸው። 参见章节 |