ኤርምያስ 33:26 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)26 በአብርሃምና በይስሐቅ በያዕቆብም ዘር ላይ ገዦች እንዲሆኑ ከዘሩ ላለመውሰድ፥ የያዕቆብንና የባርያዬን የዳዊትን ዘር እኔ ደግሞ እጥላለሁ። እኔ ምርኮአቸውን እመልሳለሁና፥ እምራቸዋለሁምና።” 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም26 የያዕቆብንና የአገልጋዬን የዳዊትን ዘር እጥላለሁ፤ ከልጆቹም በአብርሃም፣ በይሥሐቅና በያዕቆብ ዘር ላይ ገዥ እንዲሆኑ አልመርጥም፤ ይህንም የምለው ምርኳቸውን ስለምመልስና ስለምራራላቸው ነው።’ ” 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም26 የያዕቆብና የአገልጋዬን የዳዊትን ዘሮች ትቼአለሁ ማለት ነው፤ ይህም ማለት ለአገልጋዬ ለዳዊት በአብርሃም፥ በይስሐቅና በያዕቆብ ዘሮች ላይ የሚነግሥ አንድም ተወላጅ አላስነሣለትም ማለት ነው። እኔ ግን ምሕረት አደርግላቸዋለሁ፤ ንብረታቸውን እመልስላቸዋለሁ።” 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)26 እኔም ደግሞ በአብርሃምና በይስሐቅ በያዕቆብም ዘር ላይ ገዢዎች ይሆኑ ዘንድ ከዘሩ እንዳላስነሣ፥ የያዕቆብንና የባሪያዬን የዳዊትን ዘር እጥላለሁ፤ ምርኮአቸውን እመልሳለሁና፥ እምራቸውማለሁና።” 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)26 እኔም ደግሞ በአብርሃምና በይስሐቅ በያዕቆብም ዘር ላይ ገዦች ይሆኑ ዘንድ ከዘሩ እንዳልወስድ፥ የያዕቆብንና የባሪያዬን የዳዊትን ዘር እጥላለሁ፥ ምርኮአቸውን እመልሳለሁና፥ እምራቸውማለሁና። 参见章节 |