ኤርምያስ 30:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 አንተን ለማዳን ከአንተ ጋር ነኝና፥ ይላል ጌታ፤ አንተንም የበተንሁባቸውን አሕዛብን ሁሉ ፈጽሜ አጠፋለሁ፥ አንተን ግን ፈጽሜ አላጠፋህም፤ እንደጥፋትህ መጠን እቀጣሃለሁ እንጂ ያለ ቅጣት ከቶ አልተውህም። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም11 እኔ ከአንተ ጋራ ነኝ፤ አድንሃለሁም’ ይላል እግዚአብሔር፤ ‘በአሕዛብ መካከል በትኜሃለሁ፤ እነዚህን አሕዛብ ሁሉ ፈጽሜ አጠፋለሁ፤ አንተን ግን ሙሉ በሙሉ አላጠፋህም፤ በመጠኑ እቀጣሃለሁ እንጂ፣ ያለ ቅጣት አልተውህም።’ 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም11 እኔ ራሴ ከእናንተ ጋር በመሆን አድናችኋለሁ፤ እናንተን የበተንኩባቸውን አሕዛብ ሁሉ እደመስሳለሁ፤ እናንተን ግን አላጠፋም፤ ሆኖም ያለ ቅጣት አልተዋችሁም፤ የምቀጣችሁ ግን እንደ ጥፋታችሁ ነው፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ተናግሬአለሁ።” 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 አድንህ ዘንድ ከአንተ ጋር ነኝና፥ ይላል እግዚአብሔር፤ አንተንም የበተንሁባቸውን አሕዛብን ሁሉ ፈጽሜ አጠፋለሁ፤ አንተን ግን ፈጽሜ አላጠፋህም፤ በመጠን እቀጣሃለሁ፥” ያለ ቅጣትም ከቶ አልተውህም።” 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)11 አድንህ ዘንድ ከአንተ ጋር ነኝና፥ ይላል እግዚአብሔር፥ አንተንም የበተንሁባቸውን አሕዛብን ሁሉ ፈጽሜ አጠፋለሁ፥ አንተን ግን ፈጽሜ አላጠፋህም፥ በመጠን እቀጣሃለሁ፥ ያለ ቅጣትም ከቶ አልተውህም። 参见章节 |