Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 26:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 የይሁዳም አለቆች እነዚህን ነገሮች በሰሙ ጊዜ ከንጉሥ ቤት ወደ ጌታ ቤት ወጡ፥ በአዲሱም በጌታ ቤት ደጅ መግቢያ ተቀመጡ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 የይሁዳም ባለሥልጣኖች ስለ እነዚህ ነገሮች በሰሙ ጊዜ፣ ከቤተ መንግሥት ወደ እግዚአብሔር ቤት ወጡ፤ በእግዚአብሔር ቤት፣ አዲሱ በር በተባለው መግቢያ ተቀመጡ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 የይሁዳ መሪዎችም የሆነውን ነገር በሰሙ ጊዜ ከቤተ መንግሥት ወጥተው ወደ ቤተ መቅደስ መጡ፤ በቤተ መቅደሱም በአዲሱ የቅጽር በር ስፍራቸውን ያዙ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 የይ​ሁ​ዳም አለ​ቆች ይህን በሰሙ ጊዜ ከን​ጉሡ ቤት ወደ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ወጡ፤ በአ​ዲ​ሱም በእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቤት ደጅ መግ​ቢያ ተቀ​መጡ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 የይሁዳም አለቆች ይህን በሰሙ ጊዜ ከንጉሥ ቤት ወደ እግዚአብሔር ቤት ወጡ፥ በአዲሱም በእግዚአብሔር ቤት ደጅ መግቢያ ተቀመጡ።

参见章节 复制




ኤርምያስ 26:10
15 交叉引用  

ነገር ግን በየኰረብቶች ላይ የነበሩትን የአሕዛብ መሠዊያዎችን አላስወገደም፤ ሕዝቡም መሥዋዕት ማቅረባቸውንና ዕጣን ማጠናቸውን እንደ ቀጠሉ ነበር፤ የቤተ መቅደሱን ሰሜናዊ ቅጽር በር ያሠራ ይኸው ኢዮአታም ነበር።


የጌታን ቤት የላይኛውን በር ሠራ፥ በዖፌልም ቅጥር ላይ መጠነ ሰፊ ግንብ ገነባ።


ጳስኮርም ነቢዩን ኤርምያስን መታው፥ በጌታም ቤት በነበረው በላይኛው በብንያም በር ባለው በመንቈር ውስጥ አሠረው።


ንጉሡም ኢዮአቄም ኃያላኑም ሁሉ አለቆቹም ሁሉ ቃሉን በሰሙ ጊዜ ንጉሡ ሊገድለው ፈለገ፤ ኦርዮም ይህን በሰማ ጊዜ ፈርቶ ሸሸ ወደ ግብጽም ገባ።


ነገር ግን በሕዝቡ እጅ እንዳይሰጥና እንዳይገድሉት የሳፋን ልጅ የአኪቃም እጅ ከኤርምያስ ጋር ነበረች።


ወደ ቃል ኪዳኑ የገቡ አለቆች ሁሉና ሕዝቡ ሁሉ ሰምተው ማንም ሰው ወንድ ባርያውንና ሴት ባርያውን አርነት እንዲያወጣ፥ ከእንግዲህ ወዲህም ማንም እንዳይገዛቸው አደረጉ፤ እነርሱም ሰምተው አርነት አወጡአቸው።


የይሁዳን አለቆችና የኢየሩሳሌምን አለቆች እንዲሁም ጃንደረቦችንና ካህናትን በእንቦሳም ቁራጭ መካከል ያለፉትን የአገሩን ሕዝብ ሁሉ፥


ባሮክም የኤርምያስን ቃላት በላይኛው አደባባይ በጌታ ቤት በአዲሱ በር መግቢያ ባለው በጸሐፊው በሳፋን ልጅ፥ በገማርያ ጓዳ በጌታ ቤት ውስጥ በሕዝቡ ሁሉ ጆሮ ከመጽሐፉ አነበበ።


ነገር ግን ኤልናታንና ድላያ ገማርያም ክርታሱን እንዳያቃጥል ንጉሡን ቢለምኑትም እንኳ፥ እርሱ ግን አልሰማቸውም።


በውስጧ ያሉ አለቆችዋ የገደሉትን እንደሚቦጫጭቁ ተኩላዎች ናቸው። ተገቢ ያልሆነ ትርፍ ለማግኘት ሲሉ ደምን ያፈስሳሉ፥ ነፍሶችንም ያጠፋሉ።


እነሆ የእስራኤል ልዑሎች እያንዳንዱ እንደ አቅሙ ደም ሊያፈስሱ በአንቺ ውስጥ ነበሩ።


跟着我们:

广告


广告