Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 25:33 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

33 በዚያም ቀን ጌታ የገደላቸው ከምድር ዳር ጀምሮ እስከ ምድር ዳር ድረስ ይሆናሉ፤ አይለቀስላቸውም፤ በምድር ላይ እንደ ጉድፍ ይሆናሉ እንጂ አይሰበሰቡም አይቀበሩምም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

33 በዚያ ጊዜ በእግዚአብሔር የተገደሉት ከምድር ዳር እስከ ምድር ዳር በሁሉ ስፍራ ተረፍርፈው ይታያሉ፤ እንደ ጕድፍ በምድር ላይ ይጣላሉ እንጂ፣ አይለቀስላቸውም፤ ሬሳቸውም አይሰበሰብም፤ አይቀበርምም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

33 በዚያን ቀን እግዚአብሔር በሞት የሚቀጣቸው ሰዎች ሬሳ ከምድር ዳርቻ እስከ ምድር ዳርቻ ይረፈረፋል፤ የሚያለቅስላቸውም ሆነ ሰብስቦ የሚቀብራቸው አያገኙም፤ ስለዚህ እንደ ጥራጊ በሜዳ ላይ ተጥለው ይቀራሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

33 በዚ​ያም ቀን የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ግዳ​ዮች ከም​ድር ዳር ጀምሮ እስከ ምድር ዳር ድረስ ይሆ​ናሉ፤ አይ​ለ​ቀ​ስ​ላ​ቸ​ውም፤ በም​ድር ላይ እንደ ጕድፍ ይሆ​ናሉ እንጂ አይ​ሰ​በ​ሰ​ቡም፤ አይ​ቀ​በ​ሩ​ምም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

33 በዚያም ቀን የእግዚአብሔር ግዳዮች ከምድር ዳር ጀምሮ እስከ ምድር ዳር ድረስ ይሆናሉ፥ አይለቀስላቸውም፥ በምድር ላይ እንደ ጕድፍ ይሆናሉ እንጂ አይከማቹም አይቀበሩምም።

参见章节 复制




ኤርምያስ 25:33
19 交叉引用  

ከሬሳውም የሚተርፈው እንደ ፍግ በዚያ ይበተናል፤ ስለዚህም ማንም እርሷነትዋን ለይቶ በማወቅ፦ ይህች ኤልዛቤል ናት፥ ሊል አይችልም’ ያለው ነው።”


ደማቸውንም በኢየሩሳሌም ዙሪያ እንደ ውኃ አፈሰሱ፥ የሚቀብራቸውም አጡ።


እንደ ምድያምና እንደ ሲሣራ፥ በቂሶንም ወንዝ እንደ ኢያቢስ አድርግባቸው።


የጌታ ቁጣ በሕዝቡ ላይ ነዶአል፤ እጁን አንሥቶ መቶአቸዋል፤ ተራሮች ራዱ፤ ሬሳዎችም በመንገድ ላይ እንደ ተጣለ ጥራጊ ሆኑ፤ ይህ ሁሉ ሆኖ ግን ቁጣው ገና አልተመለሰም፤ እጁም እንደ ተነሣ ነው።


ጌታም በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ በእሳትና በሰይፉ ይፈርዳል፤ በጌታም ተወግተው የሞቱት ይበዛሉ።


በወደዱአቸውና ባገለገሉአቸው፥ በተከተሉአቸውና በፈለጉአቸው፥ በሰገዱላቸውም በፀሐይና በጨረቃ በሰማይም ሠራዊት ሁሉ ፊት ይዘረጉአቸዋል፤ አይሰበሰቡም አይቀበሩምም፥ በምድርም ፊት ላይ እንደ ጉድፍ ይሆናሉ።


ሰይፉ እንዲወለወል፥ በእጅም እንዲያዝ ተሰጠ፤ በገዳዩ እጅ እንዲቀመጥ ተሳለ፥ ተወለወለም።


በመንጋጋህ መንጠቆ አስገባለሁ፥ የወንዞችህን ዓሦች ከቅርፊትህ ጋር አጣብቃለሁ፤ በቅርፊትህ ከተጣበቁት የወንዞችህ ዓሦች ሁሉ ጋር ከወንዞችህ መካከል አወጣሃለሁ።


አንተንና የወንዞችህን ዓሦች ሁሉ ወደ ምድረ በዳ እጥላለሁ፤ በሜዳ ላይ ትወድቃለህ፤ አትከማችም፥ አትሰበሰብም፤ ምግብ እንድትሆን ለምድር አራዊትና ለሰማይ ወፎች እሰጥሃለሁ።


እናንተም ኢትዮጵያውያን ደግሞ፥ በሰይፌ ትገደላላችሁ።


ከወገኖችና ከነገዶችም ከቋንቋዎችም ከአሕዛብም የሆኑ ሰዎች ሦስት ቀን ተኩል በድናቸውን ይመለከታሉ፤ በድናቸውም ወደ መቃብር እንዲገባ አይፈቅዱም።


跟着我们:

广告


广告