Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 25:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ከእነርሱም የእልልታን ድምፅና የደስታን ድምፅ፥ የሙሽራውን ድምፅና የሙሽራይቱን ድምፅ፥ የወፍጮንም ድምፅ የመብራትንም ብርሃን አስቀራለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 የደስታንና የእልልታን ድምፅ፣ የሙሽራውንና የሙሽራዪቱን ድምፅ፣ የወፍጮን ድምፅና የመብራትን ብርሃን አስቀራለሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 የደስታና የሐሤት ድምፅ፥ የሠርግ ዘፈንም ድምፅ እንዳይኖር፥ ማንም ሰው እህል እንዳይፈጭ፥ ወይም በሌሊት መብራት እንዳያበራ አደርጋለሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 ከእ​ነ​ር​ሱም የሐ​ሤ​ትን ድም​ፅና የደ​ስ​ታን ድምፅ፥ የወ​ንድ ሙሽ​ራን ድም​ጽና የሴት ሙሽ​ራን ድምፅ፥ የወ​ፍ​ጮ​ንም ድምፅ የመ​ብ​ራ​ት​ንም ብር​ሃን አስ​ቀ​ራ​ለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 ከእነርሱም የእልልታን ድምፅና የደስታን ድምፅ፥ የወንድ ሙሽራን ድምፅና የሴት ሙሽራን ድምፅ፥ የወፍጮንም ድምፅ የመብራትንም ብርሃን አስቀራለሁ።

参见章节 复制




ኤርምያስ 25:10
14 交叉引用  

ወፍጮ ወስደሽ ዱቄትን ፍጪ፤ መሸፈኛሽን አውጪ ረጅሙንም ልብስሽን አውልቀሽ ጣይው፤ ባትሽን ግለጪ፥ ወንዙን ተሻገሪ።


የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላልና፦ እነሆ፥ በዓይናችሁ ፊት በዘመናችሁም፥ የእልልታን ድምፅና የደስታን ድምፅ፥ የሙሽራውን ድምፅና የሙሽራቱይን ድምፅ ከዚህ ስፍራ አስቀራለሁ።


ሐሤትና ደስታ ከፍሬያማው እርሻና ከሞዓብ ምድር ጠፍተዋል፤ የወይ ጠጁን ከወይን መጥመቂያው አጥፍቻለሁ፤ ጠማቂውም በእልልታ አይጠምቅም፥ እልልታቸውም እልልታ አይሆንም።


ምድሪቱም ባድማ ትሆናለችና ከይሁዳ ከተሞችና ከኢየሩሳሌም አደባባይ የእልልታን ድምፅና የደስታን ድምፅ፥ የሙሽራውን ድምፅና የሙሽራይቱን ድምፅ አጠፋለሁ።


የልባችን ደስታ ቀርቶአል፥ ዘፈናችን ወደ ልቅሶ ተለውጦአል።


የዘፈንሽን ብዛት አስቆማለሁ፤ የበገናሽ ድምፅ ከእንግዲህ ወዲያ አይሰማም።


ስለዚህ እህሌን በጊዜው፥ ወይን ጠጄንም በወቅቱ ፈጽሞ እወስዳለሁ፥ ዕራቁትነትዋንም መሸፈኛ የነበረውን ጥጤንና የተልባ እግሬን እገፍፋታለሁ።


跟着我们:

广告


广告