Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 23:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

7 “ስለዚህ፥ እነሆ፦ ‘የእስራኤልን ልጆች ከግብጽ ምድር ያወጣ በሕያው ጌታ እምላለሁ!’ ብለው ዳግመኛ የማይምሉበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል ጌታ፤

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

7 “ስለዚህ ሰዎች፣ ‘እስራኤላውያንን ከግብጽ ምድር ያወጣ ሕያው እግዚአብሔርን!’ ብለው ከእንግዲህ የማይምሉበት ዘመን ይመጣል ይላል እግዚአብሔር፤

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

7 “ሰዎች ‘የእስራኤልን ሕዝብ ከግብጽ ምድር ያወጣ ሕያው እግዚአብሔርን’ ብለው የማይምሉበት ጊዜ ይመጣል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

7 ስለ​ዚህ እነሆ፥ “የእ​ስ​ራ​ኤ​ልን ሕዝብ ከግ​ብፅ ምድር ያወጣ ሕያው እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን! ዳግ​መኛ የማ​ይ​ባ​ል​በት ዘመን ይመ​ጣል፥” ይላል እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

7 ስለዚህ፥ እነሆ፦ የእስራኤልን ልጆች ከግብጽ ምድር ያወጣ ሕያው እግዚአብሔርን! ዳግመኛ የማይባልበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል እግዚአብሔር፥

参见章节 复制




ኤርምያስ 23:7
9 交叉引用  

በዚያን ቀን፤ ጌታ እጁን ዘርግቶ እንደገና የተረፈውን የሕዝቡን ትሩፍ ከአሦር፤ ከታችኛው ግብጽ፤ ከላይኛው ግብጽ፤ ከኢትዮጵያ፤ ከኤላም፤ ከባቢሎን፤ ከሐማትና ከባሕር ጠረፍ ምድር ይሰበስባል።


እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ ዘርህንም ከምሥራቅ አመጣዋለሁ፥ ከምዕራብም እሰበስብሃለሁ።


የመንጋዬንም ትሩፍ ካባረርኋቸው ምድር ሁሉ ወደ በረታቸው ራሴ ሰብሰቤ እመልሳቸዋለሁ፤ እነርሱም ያፈራሉ፥ ይበዛሉም።


እነሆ፥ የሕዝቤን የእስራኤልንና የይሁዳን ምርኮ የምመልስበት ዘመን ይመጣልና፥ ይላል ጌታ፤ ለአባቶቻቸውም ወደ ሰጠኋት ምድር እመልሳቸዋለሁ፥ እነርሱም ይወርሱአታል፥ ይላል ጌታ።”


ብሬንና ወርቄን ወስዳችኋልና፥ የተወደደውንም ብርቅዬ ዕቃዎቼንም ወደ መቅደሳችሁ አስግብታችኋልና፥


ከግብጽ ምድር እንደ ወጣህበት ዘመን ተአምራትን አሳየዋለሁ።


跟着我们:

广告


广告