Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 15:20 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

20 ለዚህም ሕዝብ የተመሸገ የናስ ቅጥር አደርግሃለሁ፤ ይዋጉሃል እኔ ግን ላድንህና ልታደግህ ከአንተ ጋር ነኝና አያሸንፉህም፥ ይላል ጌታ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

20 ለዚህ ሕዝብ የናስ ቅጥር፣ የተመሸገ የናስ ቅጥር አደርግሃለሁ፤ ልታደግህና፣ ላድንህም፣ እኔ ከአንተ ጋራ ነኝና፤ ቢዋጉህም እንኳ፣ ሊያሸንፉህ አይችሉም፤” ይላል እግዚአብሔር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

20 እነርሱን መቋቋም እንድትችል እንደ ነሐስ ግንብ አበረታሃለሁ፤ አንተን ለማዳንና ለመታደግ ከአንተ ጋር ስለ ሆንኩ አደጋ ቢጥሉብህም እንኳ አያሸንፉህም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

20 ለዚ​ህም ሕዝብ የተ​መ​ሸገ የናስ ቅጥር አደ​ር​ግ​ሃ​ለሁ፤ ይዋ​ጉ​ሃል፤ እኔ ግን ለማ​ዳን ከአ​ንተ ጋር ነኝና አያ​ሸ​ን​ፉ​ህም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

20 ለዚህም ሕዝብ የተመሸገ የናስ ቅጥር አደርግሃለሁ፥ ይዋጉሃል እኔ ግን ለማዳን ከአንተ ጋር ነኝና አያሸንፉህም።

参见章节 复制




ኤርምያስ 15:20
27 交叉引用  

የጻድቃን መድኃኒታቸው በጌታ ዘንድ ነው፥ በመከራቸውም ጊዜ መጠጊያቸው እርሱ ነው።


ዕረፉ፥ እኔም አምላክ እንደሆንሁ እወቁ፥ በአሕዛብ ዘንድ ከፍ ከፍ እላለሁ፥ በምድርም ላይ ከፍ ከፍ እላለሁ።


አሕዛብ ተናወጡ መንግሥታትም ተረበሹ፥ እርሱ ቃሉን ሰጠ፥ ምድርም ተንቀጠቀጠች።


እኔ ከአንተ ጋር ነኝና አትፍራ፤ እኔ አምላክህ ነኝና አትደንግጥ፤ አበረታሃለሁ፥ እረዳሀለሁ፥ በጽድቄም ቀኝ ደግፌ እይዝሃለሁ።


ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል፤ እነሆ፤ ድንግል ትፀንሳለች፤ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፤ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።


እኔ ላድንህ ከአንተ ጋር ነኝና በእነርሱ ምክንያት አትፍራ፥ ይላል ጌታ።”


እናቴ ሆይ፥ ወዮልኝ! ለምድር ሁሉ የሙግትና የጥል ሰው የሆንሁትን ወለድሽኝ፤ ለማንም አላበደርሁም፥ ማንም ለእኔ አላበደረም፥ ነገር ግን ሁሉ ይረግመኛል።


አቤቱ! አንተ ታውቃለህ፤ አስታውሰኝ ጐብኘኝም፥ የሚያሳድዱኝንም ተበቀልልኝ፤ ቁጣህንም ከማዘግየትህ የተነሣ እንዳታጠፋኝ፤ ስለ አንተ ስድብን እንደ ታገሥሁ እወቅ።


ኤርምያስም ኢየሩሳሌም እስከ ተያዘችበት ቀን ድረስ በእስር ቤት አደባባይ ተቀመጠ።


የባቢሎንም ንጉሥ ናቡከደነፆር ስለ ኤርምያስ በዘበኞቹ አለቃ በናቡዘረዳን በኩል እንዲህ ሲል ትእዛዝን ሰጠ፦


የምትፈሩትን የባቢሎንን ንጉሥ አትፍሩት፤ እናንተን ለማዳን ከእጁም ለመታደግ እኔ ከእናንተ ጋር ነኝና እርሱን አትፍሩ፥ ይላል ጌታ።


“መንገዳቸውን እንድታውቅና እንድትፈትን በሕዝቤ መካከል አቅላጭና ፈታኝ አድርጌሃለሁ።


እነሆ፥ ፊትህን በፊታቸው ግምባርህንም በግምባራቸው አጠንክሬአለሁ።


ግምባርህን ከባልጩት እንደሚጠነክር አልማዝ አድርጌዋለሁ፥ እነርሱ ዓመፀኛ ቤት ናቸውና አትፍራቸው፥ ከፊታቸውም የተነሣ አትደንግጥ።


ጌታ ከመንፈስህ ጋር ይሁን። ጸጋ ከእናንተ ጋር ይሁን፤ አሜን።


跟着我们:

广告


广告