Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኤርምያስ 10:21 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

21 እረኞች ቂላ ቂል ሆነዋልና፥ ጌታንም አልጠየቁትምና አልተከናወነላቸውም፥ መንጎቻቸውም ሁሉ ተበትነዋል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

21 እረኞቹ አእምሮ የላቸውም፤ እግዚአብሔርን አይጠይቁም፤ ስለዚህ አልተከናወነላቸውም፤ መንጎቻቸውም ሁሉ ተበታትነዋል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

21 እኔም እንዲህ ስል መለስኩ፥ “መሪዎቻችን ሞኞች ከመሆናቸው የተነሣ፥ የእግዚአብሔርን ርዳታ አልጠየቁም፤ ውድቀት የደረሰባቸውና ሕዝባችንም ተበትኖ የቀረው ስለዚህ ነው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

21 እረ​ኞች አእ​ም​ሮ​አ​ቸ​ውን አጥ​ተ​ዋ​ልና፥ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ር​ንም አል​ፈ​ለ​ጉ​ት​ምና፤ ስለ​ዚ​ህም መሰ​ማ​ሪ​ያ​ውን አላ​ወ​ቁም፤ መን​ጎ​ቻ​ቸ​ውም ሁሉ ተበ​ት​ነ​ዋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

21 እረኞች ሰንፈዋልና፥ እግዚአብሔርን አልጠየቁትምና አልተከናወነላቸውም፥ መንጎቻቸውም ሁሉ ተበትነዋል።

参见章节 复制




ኤርምያስ 10:21
18 交叉引用  

ሰው ሁሉ ቂላ ቂልና እውቀት የሌለው ሆኖአል፥ አንጥረኛም ሁሉ ከቀረጸው ምስል የተነሣ አፍሮአል፤ ቀልጦ የተሠራ ምስሉ ውሸት ነውና፥ እስትንፋስም የላቸውምና።


በአንድ ጊዜ ቂላ ቂሎችና ሞኞች ሆነዋል፤ ጣዖታት የሚያስተምሩት ከግዑዝ እንጨት የማይሻልን ነገር ብቻ ነው።


ብዙ እረኞች የወይኑን ቦታዬን አጥፍተዋል፥ እድል ፈንታዬንም ረግጠዋል፤ የአምሮቴን እድል ፈንታ ምድረ በዳ አድርገውታል።


ካህናቱም፦ ‘ጌታ ወዴት አለ?’ አላሉም፥ የሕግ አዋቂዎች አላወቁኝም፤ ገዢዎችም ዐመፁብኝ፥ ነቢያትም በበዓል ትንቢት ተናገሩ፥ የማይረባውንም ነገር ተከተሉ።


ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ከዚህ ሰው ዘር የሚከናወንለት የለም፥ በዳዊትም ዙፋን ላይ የሚቀመጥ በይሁዳም የሚነግሥ ከእንግዲህ ወዲህ አይገኝምና፦ መካን በዘመኑም የማይከናወንለት ሰው ብላችሁ ጻፉ።”


ግመሎቻቸው ይበዘበዛሉ የእንስሶቻቸውም ብዛት ይማረካል፤ ጠጉራቸውንም ዙሪያውን የተላጩትን ሰዎች ወደ ነፋሳት ሁሉ እበትናቸዋለሁ፤ ከሁሉም አቅጣጫ ጥፋት አመጣባቸዋለሁ፥ ይላል ጌታ።


ነቢያት በሐሰት ትንቢት ይናገራሉ፥ ካህናትም በእነዚህ እጅ ይገዛሉ፥ ሕዝቤም እንዲህ ያለውን ነገር ወድደዋል፤ በፍጻሜውስ ምን ታደርጋላችሁ?


እስራኤል የባዘነ በግ ነው፤ አንበሶች አሳደዱት፤ መጀመሪያ የአሦር ንጉሥ በላው፥ በመጨረሻም የባቢሎን ንጉሥ ናቡከደነፆር አጥንቱን ቈረጠመው።


ጥበበኞች አፍረዋል ደንግጠዋል ተማርከዋልም፤ እነሆ፥ የጌታን ቃል ጥለዋል፤ ምን ዓይነት ጥበብ አላቸው?


እረኛ በተበተኑት መንጋዎቹ መካከል ሳለ መንጋውን እንደሚፈልግ፥ እንዲሁ በጎቼን እፈልጋለሁ፤ በደመናና በጨለማ ቀን፥ ከተበተኑት ስፍራ ሁሉ አድናቸዋለሁ።


ቁጣዬ በእረኞች ላይ ነዷል፥ መሪዎችንም እቀጣለሁ፤ የሠራዊት ጌታም የይሁዳን ቤት መንጋውን ጐብኝቶአል፥ በውጊያ ላይ ክብር እንደተቀዳጀ ፈረስ ያደርጋቸዋል።


ሰይፍ ሆይ፥ ባልንጀራዬ በሆነው ሰው በእረኛዬ ላይ ንቃ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ፤ በጎቹም እንዲበተኑ እረኛውን ምታ፤ እጄንም በታናናሾች ላይ አዞራለሁ።


跟着我们:

广告


广告