Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 9:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 ነገር ግን ጌታ የረአሶንን ጠላቶች ያጠናክራል፤ በእነርሱም ላይ ያመጣባቸዋል፤ ባለጋራዎቻቸውንም ያነሣሣባቸዋል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 “ጡቦቹ ወድቀዋል፤ እኛ ግን በጥርብ ድንጋይ መልሰን እንገነባለን፤ የሾላ ዛፎቹ ተቈርጠዋል፤ እኛ ግን በዝግባ እንተካለን።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 “ከጡብ የተሠሩ ግንቦች ፈርሰዋል፤ እኛ ግን እንደገና በጥርብ ድንጋይ እንገነባቸዋለን፤ ከሾላ ግንድ የተሠሩ ምሰሶዎች ተሰብረዋል፤ እኛ ግን በምርጥ የሊባኖስ ዛፍ እንተካቸዋለን።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 “ጡቡ ወደቀ፤ ነገር ግን ኑ፥ ድን​ጋይ እን​ው​ቀር፤ ሾላው ነቀዘ፤ ነገር ግን ፅድን እን​ቍ​ረጥ፤ ለራ​ሳ​ች​ንም ግን​ብን እን​ሥራ።”

参见章节 复制




ኢሳይያስ 9:10
6 交叉引用  

በግዛቱም ዘመን ሁሉ በኢየሩሳሌም ብር እንደ ድንጋይ፥ የሊባኖስ ዛፍ ብዛት በይሁዳ ኰረብቶች ግርጌ በየትኛውም ስፍራ እንደሚበቅለው ሾላ ይቆጠር ነበር።


የአካዝን ጥያቄ በመቀበል ቲግላት ፐሌሴር ዘምቶ ደማስቆን በቁጥጥሩ ሥር አደረገ፤ ንጉሥ ረጺንንም ገደለ፤ ሕዝቡንም ማርኮ ቂር ተብላ ወደምትጠራው ስፍራ ወሰደው።


እስራኤል ፈጣሪውን ረስቶአል፥ ቤተ መንግሥቶችን ሠርቶአል፤ ይሁዳም የተመሸጉትን ከተሞች አብዝቶአል፤ እኔ ግን በእርሱ ከተሞች ላይ እሳት እልካለሁ፥ የንጉሥ ቅጥሮቹንም ትበላለች።


ኤዶም፦ “እኛ ፈርሰናል፥ ነገር ግን የፈረሰውን መልሰን እንሠራለን” ቢል፥ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላል፦ “እነርሱ ይሠራሉ፥ እኔ ግን አፈርሳለሁ፤ የክፋት አገር፥ ጌታ ለዘለዓለም የተቆጣው ሕዝብ ብለው ይጠሩአቸዋል።”


በዚያችም መንገድ ማለፍ ነበረበትና ወደ ፊት ቀድሞ ሮጠና በአንድ ሾላ ላይ ወጣ።


跟着我们:

广告


广告