Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 66:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ከቶ እንዲህ ያለ ነገር ማን ሰምቶአል? እንዲህስ ያለ ነገር ማን አይቶአል? በውኑ አገር በአንድ ቀን ታምጣለችን? ወይስ በአንድ ጊዜ ሕዝብ ይወለዳል? ጽዮን እንዳማጠች ወዲያው ልጆችዋን ወልዳለችና።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 እንዲህ ያለ ነገር ማን ሰምቶ ያውቃል? እንዲህ ያለ ነገርስ ማን አይቶ ያውቃል? አገር በአንድ ጀንበር ይፈጠራልን? ወይስ ሕዝብ በቅጽበት ይገኛል? ጽዮንን ምጥ ገና ሲጀምራት፣ ልጆቿን ወዲያውኑ ትወልዳለች።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 እንዲህ ያለ ነገር የሰማ እንዲህ ያሉ ነገሮችን ያየ ማነው? አንድ አገር በአንድ ቀን፥ አንድ ሕዝብ በቅጽበት ሊወለዱ ይችላሉን? ይሁን እንጂ ጽዮን ምጥ እንደ ያዛት ወዲያውኑ ልጆችዋን ወልዳለች።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ከቶ እን​ዲህ ያለ ነገ​ርን ማን ሰም​ቶ​አል? እን​ዲ​ህስ ያለ ነገ​ርን ማን አይ​ቶ​አል? በውኑ ሀገር በአ​ንድ ቀን ታም​ጣ​ለ​ችን? ወይስ በአ​ንድ ጊዜ ሕዝብ ይወ​ለ​ዳ​ልን? ጽዮን እን​ዳ​ማ​ጠች ወዲ​ያው ልጆ​ች​ዋን ወል​ዳ​ለ​ችና።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ከቶ እንዲህ ያለ ነገር ማን ሰምቶአል? እንዲህስ ያለ ነገር ማን አይቶአል? በውኑ አገር በአንድ ቀን ታምጣለችን? ወይስ በአንድ ጊዜ ሕዝብ ይወለዳልን? ጽዮን እንዳማጠች ወዲያው ልጆችዋን ወልዳለችና።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 66:8
8 交叉引用  

ሰዎች ከጥንት ጀምሮ ማንም አልሰሙም፥ የትኛውም ጆሮ አልተቀበለውም፥ ለሚጠብቁህ ከምትሠራላችው ከአንተ አምላካችን በቀር ሌላ ማንም አላየውም።


“ስለዚህ ጌታ እንዲህ ይላል፦ በአሕዛብ መካከል፦ እንዲህ ያለ ነገር ማን ሰምቶአል? ብላችሁ ጠይቁ። የእስራኤል ድንግል በጣም የሚያስደነግጠውን ነገር አድርጋለች።


ቃሉንም የተቀበሉ ተጠመቁ፤ በዚያም ቀን ሦስት ሺህ የሚያህል ነፍስ ተጨመሩ፤


እነርሱም በሰሙ ጊዜ እግዚአብሔርን አመሰገኑ፤ አሉትም “ወንድም ሆይ! በአይሁድ መካከል አምነው የነበሩት ስንት አእላፋት እንደ ሆኑ ታያለህ፤ ሁላቸውም ለሕግ የሚቀኑ ናቸው።


ነገር ግን ቃሉን ከሰሙት ብዙዎች አመኑ፥ የወንዶችም ቍጥር አምስት ሺህ ያህል ሆነ።


ነገር ግን እንደተጻፈው፥ “ዐይን ያላየውን፤ ጆሮም ያልሰማው፤ በሰውም ልብ ያልታሰበው፤ እግዚአብሔር ለሚወዱት ያዘጋጀው፤”


跟着我们:

广告


广告