Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 65:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 እነርሱ ከነልጆቻቸው የእግዚአብሔር ቡሩካን ዘር ናቸውና በከንቱ አይደክሙም ለጥፋትም አይወልዱም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 ድካማቸው በከንቱ አይቀርም፤ ዕድለ ቢስ ልጆችም አይወልዱም፤ እነርሱና ዘራቸው፣ እግዚአብሔር የባረከው ሕዝብ ይሆናሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 ሥራቸው ከንቱ አይሆንም፤ የወለዱአቸው ልጆችና የልጅ ልጆቻቸው በእግዚአብሔር የተባረኩ ስለሚሆኑ ልጆቹን የሚወልዱት ጥፋት እንዲደርስባቸው አይደለም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 እነ​ርሱ ከእ​ነ​ል​ጆ​ቻ​ቸው የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ቡሩ​ካን ዘር ናቸ​ውና በከ​ንቱ አይ​ደ​ክ​ሙም፤ ለር​ግ​ማ​ንም አይ​ወ​ል​ዱም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 እነርሱ ከነልጆቻቸው የእግዚአብሔር ቡሩካን ዘር ናቸውና በከንቱ አይደክሙም ለጥፋትም አይወልዱም።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 65:23
28 交叉引用  

ታላቅ ሕዝብም አደርግሃለሁ፥ እባርክሃለሁ፥ ስምህንም አከብረዋለሁ፥ ለበረከትም ትሆናለህ፤


ቃል ኪዳኔንም በእኔና በአንተ መካከል ከአንተም በኋላ ከዘርህ ጋር በትውልዳቸው ለዘለዓለም ኪዳን አቆማለሁ፥ ለአንተና ከአንተ በኋላ ለዘርህ አምላክ እሆን ዘንድ።


ዘራቸው ከእነርሱ ጋር ጸንቶ ይኖራል፥ ልጆቻቸውም በዓይናቸው ፊት ናቸው።


በተጠማ ላይ ውኃን በደረቅም መሬት ላይ ፈሳሾችን አፈሳለሁና፤ መንፈሴን በዘርህ ላይ በረከቴንም በልጆችህ ላይ አፈሳለሁ፥


እኔ ግን፦ “በከንቱ ደከምሁ፥ ምንም ጥቅም ለሌለውና ለከንቱ ጉልበቴን ፈጀሁ፤ ፍርዴ ግን በጌታ ዘንድ፥ ዋጋዬም በአምላኬ ዘንድ ነው” አልኩ።


እንጀራ ላልሆነ ነገር ገንዘብን ለምን ታባክናላችሁ፥ የድካማችሁንም ዋጋ በማያጠግብ ነገር ለምን ትለውጣላችሁ? አድምጡኝ፥ በረከትንም ብሉ፥ ሰውነታችሁም በጮማ ደስ ይበለው።


ዘራቸውም በአሕዛብ መካከል፥ ልጆቻቸውም በወገኖች መካከል የታወቁ ይሆናሉ፤ ያያቸው ሁሉ ጌታ የባረከው ዘር እንደ ሆኑ ይገነዘባል።


እኔ የምሠራቸው አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር ከፊቴ ጸንተው እንደሚኖሩ፥ እንዲሁ ዘራችሁና ስማችሁ ጸንተው ይኖራሉ፥ ይላል ጌታ።


ከርኩሰታችሁ ሁሉ አድናችኋለሁ፤ እህሉን እጠራዋለሁ አበዛዋለሁም፥ ረኃብም አላመጣባችሁም።


ጉልበታችሁም በከንቱ ያልቃል፤ ምድራችሁም የተትረፈረፈውን ምርትዋን አትሰጥም፥ የምድሪቱም ዛፎች ፍሬያቸውን አይሰጡም።


በመካከላችሁም የዱር አራዊትን እለቅባችኋለሁ፤ ልጆቻችሁንም ይነጥቁአችኋል፥ እንሰሶቻችሁንም ያጠፉባችኋል፥ እናንተንም ቁጥራችሁን ያመነምኑታል፤ መንገዶቻችሁም የተራቈቱ ይሆናሉ።


የወንዶች ልጆቻችሁንም ሥጋ ትበላላችሁ፤ የሴቶች ልጆቻችሁንም ሥጋ ትበላላችሁ።


ብዙ ዘራችሁ፥ ጥቂትም አገባችሁ፤ በላችሁ፥ ነገር ግን አልጠገባችሁም፤ ጠጣችሁ፥ ነገር ግን አልሰከራችሁም፤ ለበሳችሁ፥ ነገር ግን አልሞቃችሁም፤ ደመወዙን የተቀበለ ሰው በቀዳዳ ከረጢት ለማስቀመጥ ደመወዙን ተቀበለ።


ዘር በጎተራ አሁንም አለን? ወይንና የበለስ ዛፍ ሮማንና የወይራ ዛፍ አላፈሩም፤ ከዚህች ቀን ጀምሬ እባርካችኋለሁ።


በቤቴ ውስጥ መብል እንዲሆን አሥራቱን ሁሉ ወደ ጎተራ አስገቡ፤ የሰማያቶችን መስኮቶች ባልከፍትላችሁ፥ በረከትንም አትረፍርፌ ባላፈስስላችሁ በዚህ ፈትኑኝ፥ ይላል የሠራዊት ጌታ።


የተስፋው ቃል ለእናንተና ለልጆቻችሁ ጌታ አምላካችንም ወደ እርሱ ለሚጠራቸው በሩቅ ላሉ ሁሉ ነውና፤” አላቸው።


ስለዚህ በእምነት የሆነው፥ ተስፋው በእምነት እንዲያርፍና ለዘሩ ሁሉ እንዲሆን ነው፥ ይህም ሕግ ፈፃሚዎች ብቻ ሳይሆኑ የአብርሃምን እምነት የሚጋሩትንም ጭምር ነው፥ እርሱ የሁላችንም አባት ነውና፥


ስለዚህ፥ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ጸንታችሁ ቁሙ፤ በምንም ነገር አትናወጡ። ድካማችሁ በጌታ ከንቱ ሆኖ እንደማይቀር በማወቅ፥ ለጌታ ሥራ ዘወትር የምትተጉ ሁኑ።


የክርስቶስ ከሆናችሁ ስለዚህ የአብርሃም ዘር ናችሁ፥ በተስፋውም ቃል መሠረት ወራሾች ናችሁ።


跟着我们:

广告


广告