Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 60:22 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

22 ታናሹ ለሺህ፥ የሁሉም ታናሹ ኃያል መንግሥት ይሆናል፤ እኔ ጌታ በዘመኑ ይህን በፍጥነት አደርገዋለሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

22 ከአንቺ ታናሽ የሆነው ሺሕ፣ ከሁሉም የመጨረሻው ታናሽ ኀያል መንግሥት ይሆናል፤ እኔ እግዚአብሔር ነኝ፤ ጊዜውም ሲደርስ ይህን በፍጥነት አደርጋለሁ።”

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

22 ከእነርሱ ጥቂቶቹ በሺህ የሚቈጠር ብዛት ይኖራቸዋል፤ ከእነርሱም ደካሞች የነበሩት ኀያል ሕዝብ ይሆናሉ፤ እኔ እግዚአብሔር ይህን ጉዳይ በጊዜው ፈጥኖ እንዲፈጸም አደርጋለሁ።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

22 ታናሹ ሺህ፥ የሁ​ሉም ታናሽ ታላቅ ሕዝብ ይሆ​ናል፤ እኔ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር በዘ​መ​ና​ቸው ሁሉ እሰ​በ​ስ​ባ​ቸ​ዋ​ለሁ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

22 ታናሹ ለሺህ የሁሉም ታናሹ ለብርቱ ሕዝብ ይሆናል፥ እኔ እግዚአብሔር በዘመኑ ይህን አፋጥነዋለሁ።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 60:22
15 交叉引用  

እስራኤል ሆይ፤ ሕዝብህ እንደ ባሕር አሸዋ ቢሆንም፤ የተረፉት ብቻ ይመለሳሉ። ታላቅና ጻድቅ የሆነ ጥፋት ታውጆአል።


በዐይናችን እንድናይ እግዚአብሔር ይቸኩል፤ ሥራውንም ያፋጥን፤ የእስራኤልን ቅዱስ፤ የእርሱን ዕቅድ እንድናውቃት ትቅረብ፤ ትምጣም ለሚሉ ወዮላቸው!”


ወደ አባታችሁ ወደ አብርሃም፥ ወደ ወለደቻችሁም ወደ ሳራ ተመልከቱ፤ አንድ ብቻውን በሆነ ጊዜ ጠራሁት፥ ባረክሁትም አበዛሁትም።


ከቶ እንዲህ ያለ ነገር ማን ሰምቶአል? እንዲህስ ያለ ነገር ማን አይቶአል? በውኑ አገር በአንድ ቀን ታምጣለችን? ወይስ በአንድ ጊዜ ሕዝብ ይወለዳል? ጽዮን እንዳማጠች ወዲያው ልጆችዋን ወልዳለችና።


አንካሳይቱን ትሩፍ፥ የተጣለችውን ብርቱ መንግሥት አደርጋታለሁ፤ ከአሁን ጀምሮ እስከ ዘለዓለም በጽዮን ተራራ ጌታ በእነርሱ ላይ ይነግሣል።


ራእዩ ገና እስከ ተወሰነው ጊዜ ነው፥ ወደ ፍጻሜውም ይፈጥናል፥ እርሱም አይዋሽም፤ ቢዘገይም በእርግጥ ይመጣልና ጠብቀው፤ አይዘገይም።


እግዚአብሔር ታዲያ ቀንና ሌሊት ወደ እርሱ ለሚጮኹ፥ ለሚታገሣቸውም ምርጦቹ አይፈርድላቸውምን?


ቃሉንም የተቀበሉ ተጠመቁ፤ በዚያም ቀን ሦስት ሺህ የሚያህል ነፍስ ተጨመሩ፤


ሕዝቡ ግን ያከብሩአቸው ነበር፤ የሚያምኑትም ከፊት ይልቅ ለጌታ ይጨመሩለት ነበር፤ ወንዶችና ሴቶችም ብዙ ነበሩ።


የእግዚአብሔርን ፈቃድ አድርጋችሁ የተሰጣችሁን የተስፋ ቃል እንድታገኙ ጽናት ያስፈልጋችኋል።


ወዳጆች ሆይ! እናንተ ግን በጌታ ዘንድ አንድ ቀን እንደ ሺህ ዓመት፥ ሺህ ዓመትም እንደ አንድ ቀን እንደሆነ ይህን አንድ ነገር አትርሱ።


ከዚህ በኋላ አየሁ፤ እነሆም ማንም ሊቆጥራቸው የማይችል እጅግ ብዙ ሰዎች ከሕዝብና ከነገድ ከወገንም ከቋንቋም ሁሉ ነበሩ፤ ነጭ ልብስም ለብሰው የዘንባባንም ዝንጣፊዎች በእጆቻቸው ይዘው በዙፋኑና በበጉ ፊት ቆሙ፤


跟着我们:

广告


广告