Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 60:19 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

19 ከዚያ በኋላ ጌታ የዘለዓለም ብርሃንሽ፥ አምላክሽም ክብርሽም ይሆናልና በቀን ብርሃንሽ ፀሐይ መሆኑ ይቀራል፤ የጨረቃም ብርሃን በሌሊት አያስፈልግሽም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

19 ከእንግዲህ በቀን የፀሓይ ብርሃን አያስፈልግሽም፤ በሌሊትም የጨረቃ ብርሃን አያበራልሽም፤ እግዚአብሔር የዘላለም ብርሃን፣ አምላክሽም ክብርሽ ይሆናልና።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

19 “ከእንግዲህ ወዲህ ፀሐይ በቀን፥ ጨረቃም በሌሊት አያበሩልሽም፤ ነገር ግን እግዚአብሔር ብርሃንሽ፥ አምላክሽም ክብርሽ ይሆናል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

19 ፀሐይ በቀን የሚ​ያ​በ​ራ​ልሽ አይ​ደ​ለም፤ በሌ​ሊ​ትም ጨረቃ የሚ​ወ​ጣ​ልሽ አይ​ደ​ለም፤ ለአ​ን​ቺስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የዘ​ለ​ዓ​ለም ብር​ሃ​ንሽ፥ አም​ላ​ክ​ሽም ክብ​ርሽ ይሆ​ናል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

19 ከዚያ በኋላ እግዚአብሔር የዘላለም ብርሃንሽ፥ አምላክሽም ክብርሽ ይሆናልና ፀሐይ በቀን ብርሃን አይሆንልሽም፥ የጨረቃም ብርሃን በሌሊት አያበራልሽም።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 60:19
21 交叉引用  

ብዙ ሰዎች ነፍሴን፦ አምላክሽ አያድንሽም አልዋት።


ከቤትህ ሙላት ይጠግባሉ፥ ከተድላህም ፈሳሽ ታጠጣቸዋለህ።


የጽድቄ አምላክ ሆይ በጠራሁህ ጊዜ መልስልኝ፥ በጭንቀቴም አሰፋህልኝ፥ ማረኝ፥ ጸሎቴንም ስማ።


እርሱ ዓለቴም መድኃኒቴም ነውና፥ እርሱ መጠጊያዬ ነው፥ አልታወክም።


ከአእላፍ ይልቅ በአደባባዮችህ አንዲት ቀን ትሻላለች፥ በክፉዎች ድንኳኖች ከመቀመጥ ይልቅ፥ በእግዚአብሔር ቤት ደጃፍ ላይ መቅረትን መረጥሁ።


ጌታ አምላክ ፀሐይና ጋሻ ነው፥ ሞገስንና ክብርን ይሰጣል፥ ጌታ በቅንነት የሚሄዱትን ከመልካም ነገር አያስቀራቸውም።


እናንተ የያዕቆብ ቤት ሆይ፤ ኑ፤ በጌታ ብርሃን እንመላለስ።


የሠራዊት ጌታም በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም ላይ ስለሚነግሥ በሽማግሌዎቹ ፊት ክብር ይሆናል፤ ጨረቃ ይታወካል ፀሐይም ያፍራል።


በዚያ ቀን የሠራዊት ጌታ ለቀሩት ሕዝቡ የክብር ዘውድና የጌጥ አክሊል ይሆናል፤


ጌታም የሕዝቡን ስብራት በጠገነ ዕለት፥ መቅሰፍቱ የቈሰለውንም በፈወሰ ዕለት፥ የጨረቃ ብርሃን እንደ ፀሐይ ብርሃን፥ የፀሐይም ብርሃን እንደ ሰባት ቀን ብርሃን ሰባት እጥፍ ይሆናል።


ታበጥራቸዋለህ፥ ንፋስም ይጠርጋቸዋል፥ ዐውሎ ነፋስም ይበትናቸዋል፤ አንተም በጌታ ደስ ይልሃል፥ በእስራኤልም ቅዱስ ትመካለህ።


የእስራኤልም ዘር ሁሉ በጌታ ይጸድቃሉ፥ ይመካሉም ይከብራሉም።


ጌታ የተቤዣቸው ይመለሳሉ ወደ ጽዮንም ይመጣሉ፤ የዘለዓለምም ደስታ በራሳቸው ላይ ይሆናል፤ ደስታንና ተድላን ያገኛሉ፥ ኀዘንና ልቅሶም ይሸሻል።


ብርሃንሽ መጥቶአልና፥ የጌታም ክብር ወጥቶልሻልና ተነሺ፥ አብሪ።


ሕዝብን አበዛህ፤ ደስታቸውንም ጨመርህ፤ ሰዎች ምርትን ሲሰበስቡ፤ ምርኮንም ሲከፋፈሉ ደስ እንደሚላቸው ሁሉ፤ እነርሱም በፊትህ ደስ ይላቸዋል።


ዐይኖቼንም አነሣሁ፥ እነሆም፥ በእጁ የመለኪያ ገመድ የያዘ አንድ ሰውን አየሁ።


እኔ በዙሪያዋ የእሳት ቅጥር እሆንላታለሁ፥ በመካከሏም ክብር እሆናለሁ፥ ይላል ጌታ።”


ይህም ለአሕዛብ ሁሉን የሚገልጥ ብርሃን፥ ለሕዝብህም ለእስራኤል ክብር ነው።”


ዐይኖችህ ያዩትን እነዚህን ታላላቅና የሚያስፈሩ ነገሮችን ያደረገልህ እርሱ ክብርህ ነው፥ እርሱ አምላክህ ነው።


ለከተማይቱም የእግዚአብሔር ክብር ስለሚያበራላት፥ መብራትዋም በጉ ስለ ሆነ፥ ፀሐይ ወይም ጨረቃ እንዲያበሩላት አያስፈልጓትም ነበር።


ከእንግዲህም ወዲህ ሌሊት አይሆንም፤ ጌታ አምላክም በእነርሱ ላይ ያበራላቸዋልና የመብራት ብርሃንና የፀሐይ ብርሃን አያስፈልጋቸውም፤ ከዘለዓለምም እስከ ዘለዓለም ይነግሣሉ።


跟着我们:

广告


广告