Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 59:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

11 ሁላችን እንደ ድቦች እንጮኻለን፤ እንደ ርግብ በመቃተት እንጮኻለን፤ ፍትህን በተስፋ እንጠባበቅ ነበር እርሱ ግን የለም፤ መዳንም ከእኛ ዘንድ ርቆአል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

11 ሁላችን እንደ ድቦች እናላዝናለን፤ እንደ ርግቦችም በመቃተት እንጮኻለን፤ ፍትሕን ፈለግን፤ ግን አላገኘንም፤ ትድግናን ፈለግን፤ ነገር ግን ከእኛ ርቋል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

11 ሁላችንም እንደ ድብ በመጮኽ እንደ ርግብም ምርር ብለን በማልቅስ ፍትሕንና መዳንን ለማግኘት እንጠባበቃለን፤ እነርሱ ግን ከእኛ የራቁ ስለ ሆኑ አይገኙም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

11 እንደ ድብና እንደ ርግብ በአ​ን​ድ​ነት ይሄ​ዳሉ፤ ፍር​ድን እን​ጠ​ባ​በቅ ነበር፤ መዳ​ንም የለም፤ ከእ​ኛም ርቆ​አል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

11 ሁላችን እንደ ድቦች እንጮኻለን፥ እንደ ርግብ እንለቃቀሳለን፥ ፍርድን በተስፋ እንጠባበቅ ነበር እርሱም የለም፥ መዳንም ከእኛ ዘንድ ርቆአል።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 59:11
19 交叉引用  

በዓመፃ የሚያሳድዱኝ ቀረቡ፥ ከሕግህም ራቁ።


መድኃኒት ከኀጥኣን ሩቅ ነው፥ ሥርዓትህን አልፈለጉምና።


ወገቤ በትኩሳት ተሞልቷልና፥ ሥጋዬም ጤና የለውምና።


አቤቱ፥ ጸሎቴን አድምጥ፥ ልመናዬንም ቸል አትበል።


እግዚአብሔር የሚናገረውን እሰማለሁ፥ ወደ እብደታቸው ካልተመለሱ በቀር ጌታ ሰላምን ለሕዝቡና ለቅዱሳኑ ይናገራልና።


እንደ ጨረባና እንደ ሽመላ ተንጫጫሁ፥ እንደ ርግብም አጉረመረምሁ፤ ዐይኖቼ ወደ ላይ በማየት ደከሙ። ጌታ ሆይ፥ ተጨንቄአለሁና መከታ ሁነኝ።


ልጆችሽ ዝለዋል፤ በወጥመድ እንደ ተያዘ ሚዳቋ በየአደባባዩ ራስ ላይ ተኝተዋል፤ በጌታ ቁጣና በአምላክሽ ተግሣጽ ተሞልተዋል።


ፍትህም ወደ ኋላ ተመልሶአል፥ ጽድቅም በሩቅ ቆሞአል፤ እውነትም በአደባባይ ላይ ወድቆአልና፥ ቅንነትም ሊገባ አልቻለም።


የሰላምን መንገድ አያውቁም፤ በአካሄዳቸውም ፍትህ የለም፤ መንገዳቸውን አጣመዋል፥ የሚሄድባትም ሁሉ ሰላምን አያውቅም።


ስለዚህ ፍርድ ከእኛ ዘንድ ርቆአል፥ ጽድቅም አላገኘንም፤ ብርሃንን በተስፋ እንጠባበቅ ነበር፥ እነሆም፥ ጨለማ ሆነ፤ ጸዳልን በተስፋ እንጠባበቅ ነበር፥ ነገር ግን በጨለማ ሄድን።


ሰላምን በተስፋ ተጠባበቅን፥ መልካምም አልተገኘም፤ መፈወስን በተስፋ ተጠባበቅን፥ እነሆም፥ ድንጋጤ ሆነ።


ተወግተው ስለ ሞቱት ስለ ሕዝቤ ሴት ልጅ ሰዎች ሌሊትና ቀን እንዳለቅስ ራሴ ውኃ፥ ዓይኔም የእንባ ምንጭ በሆነልኝ!


ነፍሴን ከሰላም አራቅህ፥ በጎ ነገርን ረሳሁ።


ከእነርሱም የሚሸሹ ያመልጣሉ፥ እንደ ሸለቆ እርግቦች በተራራ ላይ ይሆናሉ፥ ሁሉም በኃጢአታቸው ላይ ያቃስታሉ።


በመኝታቸው ላይ ሆነው ያለቅሱ ነበር እንጂ በልባቸው ወደ እኔ አልጮኹም፤ ስለ እህልና ስለ ወይን ጠጅ ይሰበሰቡ ነበር፤ በእኔም ላይ ዓመፁ።


የወንዞቹ በሮች ተከፈቱ፥ ቤተ መንግሥቱም ቀለጠ።


ቆሟል፥ ተገለጠች፥ ተማረከች፥ ሴቶች አገልጋዮቿም እንደ ርግብ እየጮኹና ደረታቸውን እየመቱ አለቀሱ።


跟着我们:

广告


广告