Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 57:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 በመንገድሽም ብዛት ደከምሽ፥ ነገር ግን፦ ተስፋ የለም አላልሽም፤ የጉልበትን መታደስ አገኘሽ፥ ስለዚህም አልዛልሽም።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 በመንገድ ብዛት ደከምሽ፤ ነገር ግን ‘ተስፋ የለውም’ አላልሽም፤ የጕልበት መታደስ አገኘሽ፤ ስለዚህም አልዛልሽም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ከብዙ መንከራተታችሁ የተነሣ ትደክማላችሁ፤ ሆኖም ግን ፍላጎታችሁ በጣም ስለ ተነሣሣ “ጠቃሚ አይደለም” ብላችሁ አላቆማችሁም።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 በመ​ን​ገ​ድ​ሽም ብዛት ደከ​ምሽ፤ ዳግ​መ​ኛም ጕል​በት እያ​ለኝ ከእ​ን​ግ​ዲህ ወዲህ ይህን መን​ገድ አል​ተ​ውም አላ​ል​ሽም፤ ይህ​ንም ስላ​ደ​ረ​ግሽ አላ​ፈ​ር​ሽም።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 በመንገድሽም ብዛት ደከምሽ፥ ነገር ግን፦ ተስፋ የለም አላልሽም፥ የጕልበትን መታደስ አገኘሽ፥ ስለዚህም አልዛልሽም።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 57:10
12 交叉引用  

በምክርሽ ብዛት ደክመሻል፤ አሁንም የሰማይን ከዋክብት የሚቈጥሩ፥ ከዋክብትንም የሚመለከቱ፥ በየመባቻውም የሚመጣውን ነገር የሚናገሩ ተነሥተው ከሚመጣብሽ ነገር ያድኑሽ።


“እነርሱ ግን፦ ‘ተስፋ የለውም! አሳባችንን ተከትለን እንሄዳለን፥ ሁላችንም እንደ ክፉው ልባችን እልከኝነት እናደርጋለን’ አሉ።


በባዶ እግርሽ ከመሄድ፥ ጉሮሮሽንም ከውኃ ጥም ከልክዪ፤ አንቺ ግን፦ ‘ተስፋ የለኝም፥ አይሆንም! እንግዶችን ወድጄአለሁና፥ እከተላቸዋለሁም’ አልሽ።


መንገድሽን ለመለወጥ ለምን በጣም ትሮጫለሽ? አሦር እንዳሳፈረሽ ግብጽ እንዲሁ ያሳፍርሻል።


ስለዚህ ካፊያ ተከለከለ፥ የበልጉም ዝናብ ጠፋ፤ የጋለሞታም ሴት ፊት ቢኖርሺም እንኳ ለማፈር ግን እንቢ አልሽ።


አቤቱ! ዓይንህ እውነትን የምትመለከት አይደለችምን? አንተ ቀሥፈሃቸዋል ነገር ግን አላዘኑም፥ ቀጥቅጠሃቸዋልም ነገር ግን ተግሣጽን ለመቀበል እንቢ አሉ፤ ፊታቸውን ከድንጋይ ይልቅ አጠንክረዋል፤ ለመመለስ እንቢ አሉ።


ሰውም ሁሉ ባልንጀራውን ያታልላል በእውነትም አይናገሩም፤ ሐሰትን መናገርንም ምላሳቸው ተምሮአል፥ ክፉንም ለማድረግ ይደክማሉ።


ብዙ ለፍታ ደከመች፥ ሆኖም የዝገቱ ክምር በእሳት እንኳ አልለቀቀም።


እነሆ፥ አሕዛብ ለእሳት እንደሚሠሩ፥ ሕዝቦችም ለከንቱነት እንደሚደክሙ ከሠራዊት ጌታ ዘንድ የሆነ አይደለምን?


እኔም ድሮ ያለ ሕግ ሕያው ነበርሁ፤ ትእዛዝ በመጣ ጊዜ ግን ኃጢአት ሕያው ሆነ።


跟着我们:

广告


广告