Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 54:6 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

6 ጌታ እንደ ተተወችና እንደ ተበሳጨች በልጅነትዋም እንደ ተጣለች ሚስት ጠርቶሻል፥ ይላል አምላክሽ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

6 እንደ ተናቀች የልጅነት ሚስት፣ ከልብ እንዳዘነችና እንደ ተጠላች ሚስት፣ እግዚአብሔር እንደ ገና ይጠራሻል” ይላል አምላክሽ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

6 አንቺ በወጣትነት ዕድሜዋ አግብታ በመባረርዋ ልብዋ እንደ ተሰበረ ሴት ነሽ፤” ነገር ግን እግዚአብሔር አምላክሽ እንደገና ወደ እርሱ ጠርቶ እንዲህ ይልሻል፦

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

6 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር እንደ ተተ​ወ​ችና እንደ ተበ​ሳ​ጨች፥ በል​ጅ​ነ​ቷም እንደ ተጠ​ላች ሴት የጠ​ራሽ አይ​ደ​ለም፥ ይላል አም​ላ​ክሽ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

6 እግዚአብሔር እንደ ተተወችና እንደ ተበሳጨች በልጅነትዋም እንደ ተጣለች ሚስት ጠርቶሻል፥ ይላል አምላክሽ።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 54:6
13 交叉引用  

ምንጭህ ቡሩክ ይሁን፥ ከጉብዝናህም ሚስት ጋር ደስ ይበልህ።


በሕይወትህ፥ አንተም ከፀሐይ በታች በምትደክምበት ድካም ይህ እድል ፈንታህ ነውና ከንቱ በሆነ በሕይወትህ ዘመን ሁሉ፥ ከፀሐይ በታች በሰጠህ፥ በከንቱ ዘመንህ ሁሉ፥ ከምትወድዳት ሚስትህ ጋር ደስ ይበልህ።


ከእንግዲህ ወዲህ፦ የተተወች አትባዪም፤ ምድርሽም ከእንግዲህ ወዲህ፦ ውድማ አትባልም፤ ነገር ግን ጌታ ደስታዬ ባንቺ ነው ብሏታልና፥ ምድርሽም ባል ታገባለችና አንቺ፦ ደስታዬ የሚኖርባት ትባያለሽ ምድርሽም፦ ባል ያገባች ትባላለች።


‘ማንም የማይሻት ጽዮን!’ ‘የተጣለች’ ብለው ጠርተውሻልና እኔ ጤናሽን እመልስልሻለሁ ቁስልሽንም እፈውሳለሁ፥ ይላል ጌታ።


የበኣሊምን ስም ከአፏ አስወግዳለሁና፥ ከእንግዲህም ወዲህ በስማቸው የሚያስታውሳቸው አይኖርም።


እናንተም፦ ለምን ይህ ሆነ? ትላላችሁ። ምክንያቱም ሚስትህን አታልለሃታልና ጌታ በአንተና በልጅነት ሚስትህ መካከል ምስክር ስለ ሆነ ነው፤ እርሷም ጓደኛህና የቃል ኪዳን ሚስትህ ነበረች።


እናንተ ደካሞችና ሸክም የከበዳችሁ ሁሉ ወደ እኔ ኑ፤ እኔም አሳርፋችኋለሁ።


ነገር ግን ኀዘንተኞችን የሚያጽናና አምላክ በቲቶ መምጣት አጽናናን፤


跟着我们:

广告


广告