Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 52:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

13 እነሆ፥ አገልጋዬ በማስተዋል ያደርጋል፤ ይከብራል ከፍ ከፍም ይላል፥ እጅግ ታላቅም ይሆናል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

13 እነሆ፤ ባሪያዬ የሚያከናውነው በማስተዋል ነው፤ ገናና ይሆናል፤ ከፍ ከፍ ይላል፤ እጅግ ይከብራልም።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

13 እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ “እነሆ፥ አገልጋዬ ሥራው ሁሉ ይከናወንለታል፤ በክብርም እጅግ ከፍ ከፍ ይላል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

13 እነሆ፥ አገ​ል​ጋዬ ያስ​ተ​ው​ላል፤ ከፍ ከፍ ይላል፥ ይከ​ብ​ራ​ልም፤ እጅ​ግም ደስ ይለ​ዋል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

13 እነሆ፥ ባሪያዬ በማስተዋል ያደርጋል፥ ይከብራል ከፍ ከፍም ይላል፥ እጅግ ታላቅም ይሆናል።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 52:13
22 交叉引用  

እነሆ ደግፌ የያዝሁት አገልጋዬ፤ ነፍሴ ደስ የተሰኘችበት ምርጤ፤ በእርሱ ላይ መንፈሴን አድርጌአለሁ፤ እርሱም ለአሕዛብ ፍርድን ያወጣል።


ደሴቶች ሆይ፥ ስሙኝ፥ እናንተም በሩቅ ያላችሁ አሕዛብ፥ አድምጡ፤ ጌታ ከማኅፀን ጠርቶኛል፥ ከእናቴም ሆድ ጀምሮ ስሜን አንስቶአል፤


እርሱም፦ “እስራኤል ሆይ፥ አንተ አገልጋዬ ነህ በአንተም እከበራለሁ” አለኝ።


ስለዚህም እርሱ ብዙዎችን ይወርሳል፥ ከኃያላንም ጋር ምርኮን ይከፋፈላል፤ ነፍሱን ለሞት አሳልፎ ሰጥቶአል፥ ከዓመፀኞችም ጋር ተቈጥሮአል፤ እርሱ ግን የብዙ ሰዎችን ኃጢአት ተሸከመ፥ ስለ ዓመፀኞችም ማለደ።


ለዘለዓለም የሚኖር ስሙም ቅዱስ የሆነ፥ ከፍ ያለው ልዑል እንዲህ ይላል፦ የተዋረዱትን ሰዎች መንፈስ ሕያው አደርግ ዘንድ፥ የተቀጠቀጠውንም ልብ ሕያው አደርግ ዘንድ፥ የተቀጠቀጠና የተዋረደ መንፈስ ካለው ጋር በከፍታና በተቀደሰ ስፍራ እቀመጣለሁ።


“እነሆ፥ ለዳዊት ጻድቅ ቁጥቋጥ የማስነሣበት ዘመን ይመጣል፥ ይላል ጌታ፥ እርሱም ንጉሥ ሆኖ ይነግሣል፥ ይከናወንለታልም፥ በምድርም ፍርድንና ጽድቅን ያደርጋል።


በላያቸውም አንድ እረኛ አቆማለሁ እርሱም ያሰማራቸዋል፥ እርሱም ባርያዬ ዳዊት ነው፤ ያሰማራቸዋል እረኛም ይሆናቸዋል።


ሊቀ ካህን ኢያሱ ሆይ፥ ስማ! በፊትህም የሚቀመጡት ባልንጀሮችህ ለሚመጣው ነገር ምልክት የሚሆኑ ሰዎች ናቸውና ይስሙ! እነሆ፥ እኔ አገልጋዬን ቁጥቋጡን አወጣለሁ።


ኢየሱስም ቀረበና እንዲህ አላቸው “ሥልጣን ሁሉ በሰማይና በምድር ተሰጥቶኛል።


ከላይ የሚመጣው ከሁሉ በላይ ነው፤ ከምድር የሚሆነው የምድር ነው፥ የምድሩንም ይናገራል። ከሰማይ የሚመጣው ከሁሉ በላይ ነው።


እርሱም የክብሩ ጸዳልና የባሕርዩ ምሳሌ ሆኖ፥ ሁሉን በሥልጣኑ ቃል እየደገፈ፥ ኀጢአታችንን ካነጻ በኋላ በሰማያት በግርማው ቀኝ ተቀመጠ፤


跟着我们:

广告


广告