ኢሳይያስ 50:7 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)7 ጌታ እግዚአብሔር ይረዳኛልና አልታወክሁም፤ ስለዚህም ፊቴን እንደ ባልጩት ድንጋይ አድርጌዋለሁ፥ ኀፍረት ላይ እንደማልወድቅም አውቃለሁ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም7 ጌታ እግዚአብሔር ስለሚረዳኝ አልዋረድም፤ ስለዚህ ፊቴን እንደ ባልጩት ድንጋይ አድርጌአለሁ፤ እንደማላፍርም ዐውቃለሁ። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም7 ጌታ እግዚአብሔር ስለሚረዳኝ አልተዋረድኩም፤ ራሴን እንደ ጠንካራ ድንጋይ አበረታሁ፤ እንደማላፍርም ዐውቃለሁ። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)7 ጌታ እግዚአብሔር ረዳኝ፤ ስለዚህም አላፈርሁም፤ ፊቴንም እንደ ባልጩት ድንጋይ አድርጌዋለሁ፤ እንዳላፍርም አውቃለሁ። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)7 ጌታ እግዚአብሔር ይረዳኛልና ስለዚህ አልታወክሁም፥ ስለዚህም ፊቴን እንደ ባልጩት ድንጋይ አድርጌዋለሁ፥ እንዳላፍርም አውቃለሁ። 参见章节 |