Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 5:8 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

8 ምንም ስፍራ ለሌሎች እስከማይተርፍ ድረስ፤ ቤትን በቤት ላይ በመጨመር፤ መሬትን ከመሬት ጋር በማያያዝ፤ ለብቻችሁ በምድር ተስፋፍታችሁ ለምትኖሩ ወዮላችሁ!

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

8 ስፍራ ለሌሎች እስከማይተርፍ፣ ቤትን በቤት ላይ በመጨመር፣ መሬትን ከመሬት ጋራ በማያያዝ፣ ለብቻችሁ በምድር ተስፋፍታችሁ ለምትኖሩ ወዮላችሁ!

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

8 በአገሪቱ ላይ መኖር የሚገባችሁ እናንተ ብቻ መስሎአችሁ፥ ቀድሞ በነበራችሁ ይዞታ ላይ ለመቀላቀል ሰዎችን ሁሉ እያስወጣችሁ ቤትን ከቤት ማያያዝና እርሻንም በእርሻ ላይ ለመቀላቀል ለምትፈልጉ ወዮላችሁ!

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

8 ከጎ​ረ​ቤ​ቶ​ቻ​ቸው እርሻ ይወ​ስዱ ዘንድ፥ ምድ​ር​ንም ለብ​ቻ​ቸው ይይ​ዟት ዘንድ፥ ቤትን ከቤት ጋር ለሚ​ያ​ያ​ይዙ፥ እር​ሻ​ንም ከእ​ርሻ ጋር ለሚ​ያ​ቀ​ራ​ርቡ ወዮ​ላ​ቸው!

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

8 ስፍራ እስከማይቀር ድረስ እናንተም በምድር ላይ ብቻችሁን እስክትቀመጡ ድረስ፥ ቤትን ከቤት ጋር ለሚያያይዙ እርሻን ከእርሻ ጋር ለሚያቀራርቡ ወዮላቸው!

参见章节 复制




ኢሳይያስ 5:8
14 交叉引用  

በተደመሰሱም ከተሞች ውስጥ፥ ሰውም በሌለባቸው፥ ክምር ለመሆን በተመደቡ ቤቶች ውስጥ ተቀምጦአልና


እርሱ ከበላ በኋላ ምንም አልተረፈም፥ ስለዚህ በረከቱም አይጸናም።


ትርፍ ለማግኘት የሚሳሳ ሰው የራሱን ቤት ያውካል፥ መማለጃን የሚጠላ ግን በሕይወት ይኖራል።


የሰው ልጅ ሆይ፥ ወንድሞችህ፥ ዘመዶችህ፥ የእስራኤልም ቤት ሁሉ፥ በኢየሩሳሌም ለሚኖሩ ሁሉ፥ “ከጌታ ራቁ፥ ምድሪቱ ርስት ሆና ለእኛ ተሰጥታለች” ብለዋል።


የሰው ልጅ ሆይ፥ በእስራኤል ምድር ባሉ ፍርስራሽ ስፍራዎች የሚኖሩ፦ አብርሃም ብቻውን ሳለ ምድሪቱን ወረሰ፤ እኛ ደግሞ ብዙዎች ነን ምድሪቱም ርስት ሆና ለእኛ ተሰጥታለች ይላሉ።


ጌታ እንዲህ ይላል፦ “ዳርቻቸውን ለማስፋት ሲሉ የገለዓድን እርጉዞች ቀድደዋልና ስለ ሦስት የአሞን ልጆች ኃጢአት ስለ አራትም መቅሠፍቴን ከማድረግ አልመለስም።


ክፋትን ለማድረግ በምስጢር ለሚያቅዱና በመኝታቸው ላይ ክፋ ነገርን ለሚሠሩ ወዮላቸው! ሲነጋ ይፈጽሙታል፥ ኃይል በእጃቸው ነውና።


የእርሻ ቦታዎችን ይመኛሉ፥ ይይዟቸዋልም፤ ቤቶችንም፥ ይወስዷቸዋልም፤ ሰውንና ቤቱን፥ ሰውንና ውርሱን ይጨቁናሉ።


እነዚህ ሁሉ፦ ለእርሱ ያልሆነውን ወደ እርሱ ለሚሰበስብ መያዣውንም ለራሱ የሚያበዛ ወዮለት! እስከ መቼ ነው? እያሉ ምሳሌ አይመስሉበትምን?


“እናንተ ግብዞች ጻፎችና ፈሪሳውያን! መንግሥተ ሰማያትን በሰዎች ፊት ስለምትዘጉ ወዮላችሁ፤ እናንተ ራሳችሁ አትገቡም፤ የሚገቡትንም እንዳይገቡ ትከለክላላችሁ።


跟着我们:

广告


广告