Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 5:23 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

23 ጉቦን በመቀበል በደለኛን ንጹሕ ለሚያደርጉ፤ ለበደል አልባ ሰው ፍትሕን ለሚነፍጉ ወዮላቸው!

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

23 ጕቦን በመቀበል በደለኛን ንጹሕ ለሚያደርጉ፣ ለበደል አልባ ሰው ፍትሕን ለሚነፍጉ ወዮላቸው!

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

23 ጉቦ ተቀብለው በደል የሠራውን ሰው ነጻ በመልቀቅ፥ በደል የደረሰበትን ሰው ፍትሕ ለሚነፍጉ ወዮላቸው!

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

23 በደ​ለ​ኛ​ውን ስለ ጉቦ ጻድቅ ለሚ​ያ​ደ​ርጉ፥ የጻ​ድ​ቁ​ንም ጽድቅ ለሚ​ያ​ስ​ወ​ግ​ዱ​በት ወዮ​ላ​ቸው!

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

23 በደለኛውን ስለ ጉቦ ጻድቅ ለሚያደርጉ፥ የጻድቁንም ጽድቅ ለሚያስወግዱበት ወዮላቸው!

参见章节 复制




ኢሳይያስ 5:23
22 交叉引用  

እነሆም፥ ነቢይ ወደ እስራኤል ንጉሥ ወደ አክዓብ ቀርቦ፦ “እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ‘ይህን ብዙ ጭፍራ ሁሉ ታያለህን? እነሆ፥ ዛሬ በእጅህ አሳልፌ እሰጠዋለሁ፥ እኔም እግዚአብሔር እንደሆንሁ ታውቃለህ’ አለ።”


እንግዲህ አሁን ጌታን መፍራት በእናንተ ላይ ይሁን፤ በአምላካችንም በጌታ ዘንድ በደልና ለሰው ፊት ማድላት መማለጃም መውሰድ የለምና ሁሉንም ነገር ተጠንቅቃችሁ አድርጉ።”


የጻድቅን ነፍስ ያደቡባታል፥ በንጹሕ ደም ላይም ይፈርዳሉ።


ኀጥኡን የሚያጸድቅና በጻድቁ ላይ የሚፈርድ፥ ሁለቱ በጌታ ዘንድ አስጸያፊዎች ናቸው።


ኀጥእ የፍርድን መንገድ ለማጥመም ከብብት መማለጃን ይወስዳል።


ክፉዉን፦ “ጻድቅ ነህ” የሚለውን ወገኖች ይረግሙታል አሕዛብም ይጠሉታል፥


ገዥዎችሽ ዐመፀኞችና የሌባ ግብረ ዐበሮች ናቸው፤ ሁሉም ጉቦን ይወዳሉ፤ እጅ መንሻንም በብርቱ ይፈልጋሉ፤ አባት ለሌላቸው አይቆሙም፤ የመበለቶችንም አቤቱታ አይሰሙም።


ፍትሕ የጐደለውን ሕግ ለሚያወጡ፤ ጭቈና የሞላበትን ሥርዓት ለሚደነግጉ ወዮላቸው!


የድኾችን መብት ለሚገፉ፤ የተጨቈነውን ሕዝቤን ፍትሕ ለሚያዛቡ፤ መበለቶችን ለሚበዘብዙ፤ ወላጅ የሌላቸውን ልጆች ለሚመዘብሩ ወዮላቸው!


እነዚህ ደግሞ ከወይን ጠጅ የተነሣ ይስታሉ፤ ከሚያሰክርም መጠጥ የተነሣ ይንገዳገዳሉ፤ ካህኑና ነቢዩ ከሚያሰክር መጠጥ የተነሣ ይስታሉ፥ በወይን ጠጅም ይቀባዥራሉ፥ ከሚያሰክርም መጠጥ የተነሣ ይንገዳገዳሉ፤ ራእይ ሲያዩ ይስታሉ፥ በፍርድም ይሰናከላሉ።


እነርሱም ሰውን በነገር በደለኛ የሚያደርጉ፥ በበርም ለሚገሥጸው አሽክላ የሚያኖሩ፥ ጻድቁንም በከንቱ ነገር የሚያስቱ ናቸው።


የሸንጋይ ሽንገላ ክፉ ናት፤ የችግረኛም አቤቱታ ትክክል ቢሆንም እንኳን በሐሰት ቃል ድሀውን ለማጥፋት ክፉን አሳብ ያስባል።


እውነትም ታጥቶአል፥ ከክፋትም የራቀ ሰው ተበዝባዥ ሆኗል። ጌታም አየ፥ ፍትህም ስለ ሌለ ተከፋ።


ጻድቁን የምታሠቃዩ፥ ጉቦንም የምትቀበሉ፥ በበሩም አደባባይ የችግረኛውን ፍርድ የምታጣምሙ እናንተ ሆይ! በደላችሁ እንዴት እንደ በዛ፥ ኃጢአታችሁም እንዴት እንደ ጸና እኔ አውቃለሁና።


አለቆችዋ በጉቦ ይፈርዳሉ፥ ካህናቷ በክፍያ ያስተምራሉ፥ ነቢዮችዋ በብር ያሟርታሉ፤ “ጌታ በመካከላችን አይደለምን? ክፉ ነገር በእኛ ላይ አይመጣብንም” እያሉ በጌታ ይደገፋሉ።


እጆቻቸው ክፉ ለማድረግ የተለማመዱ ናቸው፤ ልዑሉና ፈራጁ ጉቦን ይፈልጋሉ፥ ትልቁም ሰው እንደ ነፍሱ ምኞት ይናገራል፤ እንዲሁም ክፋትን ይጐነጉናሉ።


በዚህም ምክንያት ከጻድቁ ከአቤል ደም ጀምሮ በቤተ መቅደሱና በመሠዊያው መካከል እስከ ገደላችሁት እስከ በራክዩ ልጅ እስከ ዘካርያስ ደም ድረስ በምድር ላይ የፈሰሰው ጻድቅ ደም ሁሉ በእናንተ ላይ ይደርሳል።


ፍርድ አታዛባ፤ አድልዎ አታድርግ፤ ጉቦ የጠቢባንን ዐይን ያሳውራል፤ የጻድቃንንም ቃል ያጣምማልና ጉቦም አትቀበል።


እናንተን ያልተቃወመውን ጻድቁን ሰው ፈረዳችሁበት፤ ገደላችሁትም።


跟着我们:

广告


广告