Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 44:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 የዝግባን ዛፎች ይቈርጣል፤ የዞጲንና የኮምቦልን ዛፍ ይመርጣል፥ ከዱር ዛፎችም መካከል እንዲጠነክር ይተወዋል፤ የጥድንም ዛፍ ይተክላል፥ ዝናብም ያበቅለዋል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 ዝግባ ይቈርጣል፤ ሾላ ወይም ወርካ ይመርጣል፤ በደን ውስጥ ካሉት ዛፎች ጋራ እንዲያድግ ይተወዋል፤ ወይም ጥድን ይተክላል፤ ያንም ዝናም ያሳድገዋል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ይህን ለማድረግ የሊባኖስ ዛፍ ወይም ዝግባ ዛፍ ወይም ዋርካ ከጫካው ይመርጣል፤ አለበለዚያም በአናጢው ተተክሎ የዝናብ ውሃ እየጠጣ የሚያድገውን የኮምበል ዛፍ ይተክላል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ያበ​ቀ​ለ​ውን፥ በዝ​ና​ምም ያሳ​ደ​ገ​ውን ዛፍ ከዱር ይቈ​ር​ጣል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 የዝግባን ዛፎች ይቈርጣል፥ የዞጲንና የኮምቦልን ዛፍ ይመርጣል፥ ከዱር ዛፎችም መካከል ይጠነክር ዘንድ ይተወዋል፥ የጥድንም ዛፍ ይተክላል ዝናብም ያበቅለዋል።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 44:14
6 交叉引用  

ለዚህ መባዕ ገንዘቡ ያልበቃው ድሀ የማይነቅዘውን እንጨት ይመርጣል፤ ምስሉም እንዳይናወጥ ያቆመው ዘንድ ብልህ ሠራተኛን ይፈልጋል።


ጠራቢው ገመድ ይዘረጋል፥ በጠመኔም ምልክት ያኖራል፥ በመሮም ይቀርጸዋል፥ በመለኪያም ይለከዋል፤ በቤትም ውስጥ እንዲቀመጥ በሰው አምሳልና በሰው ውበት ይቀርጸዋል።


ለሰውም ማገዶ ይሆናል፤ ከእርሱም ወስዶ ይሞቃል፥ አንድዶም እንጀራ ይጋግርበታል፤ ከእርሱም አምላክ አበጅቶ ይሰግድለታል፤ የተቀረጸውንም ምስል ሠርቶ በእርሱ ፊት ይንበረከካል።


የዝሙት መንፈስ አስቶአቸዋልና፥ እነርሱም ከአምላካቸው ርቀው አመንዝረዋልና ሕዝቤ ግዑዝ እንጨታቸውን ይጠይቃሉ፥ በትራቸውም ይመልስላቸዋል።


እንጨቱን “ንቃ” ዝም ያለውንም ድንጋይ “ተነሣ” ለሚለው ወዮለት! ይህ ያስተምራልን? እነሆ፥ በወርቅና በብር ተለብጦአል፥ በውስጡም ምንም እስትንፋስ የለበትም።


跟着我们:

广告


广告