ኢሳይያስ 42:13 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)13 ጌታ እንደ ኃያል ይወጣል እንደ ሰልፈኛም ቅንዓትን ያስነሣል፤ ይጮኻል ድምፁንም ያሰማል በጠላቶቹም ላይ ይበረታል። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም13 እግዚአብሔር እንደ ኀያል ሰው ይዘምታል፤ እንደ ተዋጊ በቅናት ይነሣል፤ የቀረርቶ ጩኸት ያሰማል፤ ጠላቶቹንም ድል ያደርጋል። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም13 እግዚአብሔር እንደ ጀግና ወታደር ይወጣል፤ ድምፁንም ከፍ አድርጎ ጦርነትን ያውጃል፤ በጠላቶቹም ላይ ድልን ይጐናጸፋል። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)13 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ይወጣል፤ ኀይለኛውንም ያጠፋል፤ ቅንአትንም ያስነሣል፤ በጠላቶቹም ላይ በኀይል ይጮኻል። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)13 እግዚአብሔር እንደ ኃያል ይወጣል እንደ ሰልፈኛም ቅንዓትን ያስነሣል፥ ይጮኻል ድምፁንም ያሰማል በጠላቶቹም ላይ ይበረታል። 参见章节 |