ኢሳይያስ 38:11 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)11 ደግሞም፦ በሕያዋን ምድር ጌታን አላይም፤ በዓለምም የሚኖሩትን ሰዎች ከእንግዲህ አልመለከትም አልኩ። 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም11 እንዲህም አልሁ፤ “ዳግም እግዚአብሔርን፣ እግዚአብሔርን በሕያዋን ምድር አላይም፤ ከእንግዲህም የሰውን ዘር አላይም፤ በዚህ ዓለም ከሚኖሩትም ጋራ አልሆንም። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም11 ሕያዋን በሚኖሩበት በዚህ ዓለም እግዚአብሔርን ወይም ከሕያው ፍጡር ሁሉ መካከል ሰውን ዳግመኛ አላይም ብዬ ነበር። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)11 ደግሞም፦ በሕያዋን ምድር የእግዚአብሔርን ማዳን፤ የእስራኤልንም መዳን በምድር ላይ አላይም፤ ከዘመዶችም ሰውን አላይም። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)11 ደግሞም፦ በሕያዋን ምድር እግዚአብሔርን አላይም፥ በዓለምም ከሚኖሩ ጋር ሰውን እንግዲህ አልመለከትም አልሁ። 参见章节 |