Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 36:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ራፋስቂስም እንዲህ አላቸው፦ “ለሕዝቅያስ እንዲህ ብላችሁ ንገሩት፦ ታላቁ የአሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፦ ይህ የምትተማመንበት መተማመኛ ምንድነው?

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 የጦር አዛዡም እንዲህ አላቸው፤ “ሕዝቅያስን እንዲህ በሉት፤ “ ‘ታላቁ ንጉሥ፣ የአሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፤ እስከዚህ የተማመንህበት ነገር ምንድን ነው?

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 የአሦር ባለ ሥልጣን የነበረው ራፋስ ቂስ እንዲህ አላቸው፦ “ለንጉሥ ሕዝቅያስ እንዲህ ብላችሁ ንገሩት፦ ‘እነሆ፥ የአሦር ንጉሥ የሚለው ይህ ነው፦ ለመሆኑ ይህን ያኽል ልበ ሙሉ የሆንከው በማን ተማምነህ ነው?

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ራፋ​ስ​ቂ​ስም አላ​ቸው፥ “ለሕ​ዝ​ቅ​ያስ እን​ዲህ ብላ​ችሁ ንገ​ሩት፦ ታላቁ የአ​ሦር ንጉሥ እን​ዲህ ይላል፦ በማን ትተ​ማ​መ​ና​ለህ?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ራፋስቂስም አላቸው፦ ለሕዝቅያስ እንዲህ ብላችሁ ንገሩት፦ ታላቁ የአሦር ንጉሥ እንዲህ ይላል፦ ይህ የሚትታመንበት መተማመኛ ምንድር ነው?

参见章节 复制




ኢሳይያስ 36:4
17 交叉引用  

ይህ በዚህ እንዳለ የአሦር ንጉሠ ነገሥት እንደገና የተጠናከረ ታላቅ ሠራዊት ከላኪሽ ተንቀሳቅሶ ወደ ኢየሩሳሌም በመዝመት በሕዝቅያስ ላይ አደጋ እንዲጥልበት አዘዘ፤ ያም ሠራዊት ከፍተኛ ሥልጣን ባላቸው ሦስት የጦር አዛዦቹ የሚመራ ነበር፤ እነርሱም ወደ ኢየሩሳሌም እንደ ደረሱ ከላይኛው ኲሬ ውሃ በሚተላለፍበት ቦይ አጠገብ ወደ ልብስ አጣቢዎች መስክ የሚወስደውን መንገድ ያዙ፤


ሕዝቅያስ በእስራኤል አምላክ በእግዚአብሔር ተማመነ፤ ከእርሱ በፊትም ሆነ ከእርሱ ወዲህ እርሱን የመሰለ ሌላ ንጉሥ በይሁዳ አልተነሣም፤


“የይሁዳ ንጉሥ ሕዝቅያስ ሆይ፥ የምትታመንበት አምላክ ‘ኢየሩሳሌም በአሦር ንጉሠ ነገሥት እጅ አትወድቅም’ ብሎ አያታልህ፤


እግዚአብሔርን፦ አንተ መጠጊያዬ ነህ፥ ለምን ረሳኸኝ? ጠላቶቼ ሲያስጨንቁኝ ለምን አዝኜ እመላለሳለሁ? እለዋለሁ።


ነፍሴ እግዚአብሔርን፥ ሕያው አምላክን ተጠማች፥ መቼ እደርሳለሁ? የአምላክንስ ፊት መቼ አያለሁ?


ትዕቢት ጥፋትን፥ ኩሩ መንፈስም ውድቀትን ይቀድማል።


እናንተ፦ እኛ ኃያላን በውጊያም ጽኑዓን ነን፥ እንዴት ትላላችሁ?


እነዚህ የሚያጉረመርሙ፥ የሚያማርሩ፥ ክፉ ምኞታቸውን የሚከተሉ ናቸው፤ አፋቸው የትዕቢት ቃልን ይናገራል፤ለጥቅማቸው ሲሉ ሰዎችን ያደንቃሉ።


跟着我们:

广告


广告