Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 34:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 የሰማይም ሠራዊት ሁሉ ይሟሽሻሉ፤ ሰማያትም እንደ መጽሐፍ ጥቅልል ይጠቀለላሉ፤ ሠራዊታቸው ሁሉ ከወይንና ከበለስ ላይ እንደሚረግፍ ቅጠል ይረግፋል።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 የሰማይ ከዋክብት ሁሉ ይሟሽሻሉ፤ ሰማይ እንደ ብራና ይጠቀለላል፤ የከዋክብት ሰራዊት ሁሉ፣ ጠውልጎ እንደ ረገፈ የወይን ቅጠል፣ ደርቆም እንደ ወደቀ የበለስ ቅጠል ይሆናሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ፀሐይ፥ ጨረቃና ከዋክብት ሁሉ ይጠፋሉ፤ ሰማይም እንደ ብራና ተጠቅሎ ይወገዳል፤ ከዋክብትም እንደ ወይንና እንደ በለስ ዛፍ ቅጠል ይረግፋሉ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ሰማ​ያት እንደ መጽ​ሐፍ ጥቅ​ልል ይጠ​ቀ​ለ​ላሉ፤ ከወ​ይ​ንና ከበ​ለ​ስም ቅጠል እን​ደ​ሚ​ረ​ግፍ ከዋ​ክ​ብት ሁሉ ይረ​ግ​ፋሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 የሰማይም ሠራዊት ሁሉ ይበሰብሳሉ፥ ሰማያትም እንደ መጽሐፍ ጥቅልል ይጠቀለላሉ፥ ከወይንና ከበለስም ቅጠል እንደሚረግፍ ሠራዊታቸው ሁሉ ይረግፋል።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 34:4
20 交叉引用  

የሰማይ ከዋክብትና ሠራዊታቸው፤ ብርሃን አይሰጡም፤ ፀሓይ ገና ከመውጣቷ ትጨልማለች፤ ጨረቃም ብርሃኗን አትሰጥም።


ስለዚህ በሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር መዓት፤ ቁጣው በሚነድበት ቀን፤ ሰማያትን እነቀንቃለሁ፤ ምድርንም ከስፍራዋ አናውጣለሁ።


አንተ የንጋት ልጅ አጥቢያ ኮከብ ሆይ፥ እንዴት ከሰማይ ወደቅህ! አሕዛብንም ያዋረድህ አንተ ሆይ፥ እንዴትስ ወደ ምድር ተጣልክ!


ዓይናችሁን ወደ ሰማይ አንሡ፥ ወደ ታችም ወደ ምድር ተመልከቱ፤ ሰማያትን እንደ ጢስ በንነው ይጠፋሉ፥ ምድርም እንደ ልብስ ታረጃለች፥ የሚኖሩባትም እንዲሁ ይሞታሉ፤ ማዳኔ ግን ለዘለዓለም ይሆናል፥ ጽድቄም አይፈርስም።


ምድሪቱም ከፊታቸው ትናወጣለች፥ ሰማያትም ይንቀጠቀጣሉ፥ ፀሐይና ጨረቃም ይጨልማሉ፥ ከዋክብትም ብርሃናቸውን ይሰውራሉ።


ፀሐይና ጨረቃ ጨልመዋል፥ ከዋክብትም ብርሃናቸውን ሰውረዋል።


“ከነዚያ ቀናት መከራ በኋላ ወዲያው ፀሐይ ትጨልማለች፤ ጨረቃም ብርሃንዋን አትሰጥም፤ ከዋክብትም ከሰማይ ይወድቃሉ፤ የሰማያት ኃይሎችም ይናወጣሉ።


ሰማይና ምድር ያልፋሉ፤ ቃሌ ግን አያልፍም።


ዳሩ ግን “አንድ ጊዜ ደግሜ” የሚል ቃል የማይናወጡት ጸንተው እንዲኖሩ፥ የሚናወጡት ፍጡራን ነገሮች እንደሆኑና እንደሚለወጡ ያሳያል።


ታላቅና ነጭ ዙፋን፥ በእርሱም ላይ የተቀመጠውን አየሁ፤ ምድርና ሰማይም ከፊቱ ሸሹ፤ ስፍራም አልተገኘላቸውም።


ስድስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ አየሁ፤ ታላቅም የምድር መናወጥ ሆነ፤ ፀሐይም እንደ ማቅ ጠጉር ጥቁር ሆነች፤ ጨረቃም በሞላው እንደ ደም ሆነች፤


አራተኛውም መልአክ መለከቱን ነፋ፤ የፀሐይ ሲሶና የጨረቃ ሲሶ የከዋክብትም ሲሶ ተመታ፤ የእነዚህ ሲሶ ይጨልም ዘንድ፥ የቀንና የሌሊት ሲሶው እንዳያበራ ተከለከለ።


跟着我们:

广告


广告