Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 33:17 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

17 ዐይኖችህ ንጉሡን በውበቱ ያዩታል፤ እነርሱም በሩቅ ያለች ምድርን ይመለከታሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

17 ዐይኖችህ ንጉሡን በውበቱ ያዩታል፤ በሩቅ የተዘረጋችውንም ምድር ይመለከታሉ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

17 በአራቱ ማእዘን ወሰንዋ በሰፊ ምድር ላይ ውበት ባለው ግርማ የሚያስተዳድረውን ንጉሥ ታያላችሁ፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

17 ንጉ​ሥን በክ​ብሩ ታዩ​ታ​ላ​ችሁ፤ ዐይ​ኖ​ቻ​ች​ሁም በሩቅ ያለች ምድ​ርን ያዩ​አ​ታል።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

17 ዓይኖችህ ንጉሥን በውበቱ ያዩታል፥ እነርሱም በሩቅ ያለች ምድርን ያዩአታል።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 33:17
20 交叉引用  

ብዙዎቹም ለጌታ መባ ይዘው ወደ ኢየሩሳሌም ይመጡ ነበር፥ ለይሁዳም ንጉሥ ለሕዝቅያስ እጅ መንሻ ይሰጡ ነበር፤ እርሱም ከዚህ ነገር በኋላ በአሕዛብ ሁሉ ፊት ከፍ ከፍ አለ።


እኔ ራሴ አየዋለሁ፥ ዐይኖቼም ይመለከቱታል፥ ከእኔም ሌላ አይደለም። ልቤ በመናፈቅ ዝሎአል።


መከራዬን አይተሃልና፥ ነፍሴንም ከጭንቀት አድነሃታልና በምሕረትህ ደስ ይለኛል ሐሤትም አደርጋለሁ።


ልቤ መልካም ነገርን አፈለቀ፥ እኔ ሥራዬን ለንጉሥ እነግራለሁ፥ አንደበቴ እንደ ፈጣን ጸሓፊ ብርዕ ነው።


ውዴ ብሩህና ቀይ ነው፥ ከእልፍ የተመረጠ ነው።


የሠራዊት ጌታም በጽዮን ተራራና በኢየሩሳሌም ላይ ስለሚነግሥ በሽማግሌዎቹ ፊት ክብር ይሆናል፤ ጨረቃ ይታወካል ፀሐይም ያፍራል።


ሕዝብን አበዛህ፥ አቤቱ ጌታ፥ ሕዝብን አበዛህ፤ አንተም ተከበርህ፥ የአገሪቱንም ዳርቻ ሁሉ አሰፋህ።


ጌታ ግን በእነዚያ የሰፉ ወንዞችና የመስኖች ስፍራ ሆኖ በግርማ ከእኛ ጋር ይሆናል፤ የሚቀዘፉ መርከቦች አይገቡባትም፤ ታላላቅ መርከቦች አያልፉባትም።


ጌታ ፈራጃችን ነው፥ ጌታ ሕግን ሰጪያችን ነው፥ ጌታ ንጉሣችን ነው፤ እርሱ ያድነናል።


ንጉሡ ሕዝቅያስ ይህን በሰማ ጊዜ ልብሱን ቀደደ፥ ማቅም ለበሰ፥ ወደ ጌታም ቤት ገባ።


እኔም፤ “ከንፈሮቼ የረከሱብኝ ሰው ነኝ፤ የምኖረውም ከንፈሮቹ በረከሱበት ሕዝብ መካከል ነው፤ ዐይኖቼም ንጉሡን፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርን አይቷልና ጠፍቻለሁ፤ ወዮልኝ!” አልሁ።


በጎነቱ በውበቱም እንዴት ታላቅ ነው! እህል ጎልማሶችን፥ አዲስ የወይን ጠጅም ቈነጃጅቱን ያሳምራል።


በፊታቸውም ተለወጠ፤ ፊቱ እንደ ፀሐይ አበራ፤ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ።


ቃልም ሥጋ ሆነ፤ በእኛም ዘንድ አደረ፤ ጸጋንና እውነትን የተመላውን፥ የአባቱ አንድያ ልጅ በአባቱ ዘንድ ያለውን ክብሩንም አየን።


ትእዛዜ በእርሱ ዘንድ ያለችው የሚጠብቃትንም የሚወደኝ እርሱ ነው፤ የሚወደኝንም አባቴ ይወደዋል፤ እኔም እወደዋለሁ ራሴንም እገልጥለታለሁ።”


አባት ሆይ! ዓለም ሳይፈጠር በፊት ስለ ወደድኸኝ የሰጠኸኝን ክብሬን እንዲያዩ፥ የሰጠኸኝ እነርሱ ደግሞ እኔ ባለሁበት ከእኔ ጋር ይሆኑ ዘንድ እወዳለሁ።


ስለዚህ የሚታየውን ሳይሆን የማይታየውን እንመልከት፥ ምክንያቱም የሚታየው ጊዜያዊ ነው፤ የማይታየው ግን ዘላለማዊ ነው።


ወዳጆች ሆይ፥ አሁን የእግዚአብሔር ልጆች ነን፥ ምን እንደምንሆን ገና አልተገለጠም። ቢገለጥ ግን እርሱን እንደምንመስል እናውቃለን፥ እርሱ እንዳለ እናየዋለንና።


跟着我们:

广告


广告