Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 30:25 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

25 በታላቅም እልቂት ቀን ግንቦች በወደቁ ጊዜ በረጅሙ ተራራ ሁሉ፥ ከፍ ባለውም ኮረብታ ሁሉ፥ ወንዞችና የውኃ ፈሳሾች ይወርዳሉ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

25 በታላቁ የዕልቂት ቀን ምሽጎች ሲፈርሱ፣ በረጅም ተራራ ሁሉና ከፍ ባለውም ኰረብታ ሁሉ ላይ ወራጅ ወንዝ ይፈስሳል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

25 በሕዝቡ ላይ እልቂት በሚደርስበት ጊዜ ከታላላቅ ተራራዎችና ከከፍተኛ ኰረብቶች የምንጭ ውሃ ይፈስሳል።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

25 በታ​ላ​ቅም እል​ቂት ቀን ግን​ቦች በወ​ደቁ ጊዜ፥ በረ​ዥሙ ተራራ ሁሉ ከፍ ባለ​ውም ኮረ​ብታ ሁሉ ላይ፥ ወን​ዞ​ችና የውኃ ፈሳ​ሾች ይሆ​ናሉ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

25 በታላቅም እልቂት ቀን ግንቦች በወደቁ ጊዜ እረጅሙ ተራራ ሁሉ ከፍ ባለውም ኮረብታ ሁሉ ላይ ወንዞችና የውኃ ፈሳሾች ይሆናሉ።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 30:25
22 交叉引用  

አዳራሹ ወና ይሆናል፥ በሰው የተጨናነቀውም ከተማ ወና ይሆናል፤ ምሽጉና ግንቡም ለዘለዓለም ዋሻ፥ የምድረ በዳም አህያ ደስታ፥ የመንጎችም ማሰማርያ ይሆናል።


የጌታም መልአክ ወጣ፥ ከአሦራውያንም ሰፈር መቶ ሰማንያ አምስት ሺህ ገደለ፤ ማለዳም በተነሡ ጊዜ፥ እነሆ፥ ሁሉ በድኖች ነበሩ።


በምድረ በዳ በኩል በመራቸው ጊዜ አልተጠሙም፤ ውኃንም ከዓለቱ ውስጥ አፈለቀላቸው፥ ዓለቱንም ሰነጠቀ ውኃውም ፈሰሰ።


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ እኔ ራሴ ከረጅሙ ዝግባ ጫፍ ላይ ቀንበጥን ወስጄ አስቀምጠዋለሁ፥ ከጫፎቹ አንዱን ቀንበጥ እቀነጥበዋለሁ፥ በረጅምና ከፍ ያለ ተራራም ላይ እተክለዋለሁ።


ከሕዝቦች አወጣቸዋለሁ፥ ከአገሮች እሰበስባቸዋለሁ፥ ወደ ገዛ አገራቸውም አመጣቸዋለሁ፤ በእስራኤል ተራሮች ላይ፥ በፈሳሾች አጠገብ፥ በምድሪቱም መኖሪያ በሚሆኑ ስፍራዎች ሁሉ አሰማራቸዋለሁ።


እነርሱንና በኮረብታዬ ዙሪያ ያሉትን ስፍራዎች ለበረከት አደርጋቸዋለሁ፥ ዝናቡንም በጊዜው አወርዳለሁ፤ የበረከት ዝናቦችም ይሆናሉ።


ወደ ቤቱ መግቢያ መለሰኝ፤ እነሆ ውኃ ከቤቱ መድረክ በታች ወደ ምሥራቅ ይወጣ ነበር፥ የቤቱ ፊት ወደ ምሥራቅ ይመለከት ነበርና፤ ውኃውም ከቤቱ በስተ ቀኝ በኩል በታች በመሠዊያው በደቡብ በኩል ይወርድ ነበር።


በዚያም ቀን እንዲህ ይሆናል፥ ተራሮች አዲስ ወይን ጠጅ ያንጠባጥባሉ፥ ኮረብቶችም ወተትን ያፈስሳሉ፥ በይሁዳም ያሉት ፈፋዎች ሁሉ ውኃን ያጐርፋሉ፥ ከጌታም ቤት ምንጭ ትፈልቃለች፥ የሰጢምንም ሸለቆ ታጠጣለች።


ምሽግሽ ሁሉ የመጀመሪያውን የበሰለ ፍሬ እንደ ያዙ እንደ በለስ ዛፎች ነው፤ በሚወዛወዙ ጊዜ በሚበላው አፍ ውስጥ ይወድቃሉ።


ከማድጋዎቹ ውኃ ይፈስሳል፥ ዘሩም በብዙ ውኆች ይሆናል፥ ንጉሡም ከአጋግ ይልቅ ከፍ ከፍ ይላል፥ መንግሥቱም ይከበራል።


በእኔ የሚያምን፥ መጽሐፍ እንዳለው፥ የሕይወት ውሃ ወንዝ ከሆዱ ይፈልቃል።”


ምክንያቱም የጦር ዕቃችን ሥጋዊ አይደለም፤ ምሽግን ለመስበር መለኮታዊ ኃይል አለው።


ከእግዚአብሔርና ከበጉ ዙፋን የሚወጣውን እንደ ብርሌ የሚያንጸባርቀውን የሕይወትን ውሃ ወንዝ አሳየኝ።


跟着我们:

广告


广告