ኢሳይያስ 22:2 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)2 አንቺ ጩኸትና ፍጅት የሞላብሽ ከተማ፥ የፈንጠዚያ ከተማ ሆይ፥ በአንቺ ውስጥ የተገደሉት በሰይፍ የተገደሉ አይደሉምን፥ በሰልፍስ የሞቱ አይደሉም? 参见章节አዲሱ መደበኛ ትርጒም2 አንቺ ጫጫታ የሞላብሽ ከተማ፤ የውካታና የፈንጠዝያ ከተማ ሆይ፤ የተገደሉብሽ በሰይፍ የተሠዉ አይደሉም፤ በጦርነትም አልሞቱም። 参见章节አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም2 በሁካታና በጩኸት የተሞላሽ አንቺ ከተማ ሆይ! ሰክረው በመንገዶችሽ ላይ የወደቁት ሰዎች በሰይፍ የተገደሉ ወይም በጦርነት የሞቱ አይደሉም። 参见章节የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)2 ጩኸትና ፍጅትም የተሞላብሽ ከተማ ሆይ፥ ቍስለኞችሽ በሰይፍ የቈሰሉ አይደሉም፤ በአንቺ ውስጥ የተገደሉትም በሰልፍ የተገደሉ አይደሉም። 参见章节መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)2 ጩኸትና ፍጅት የተሞላብሽ ከተማ፥ ደስታ ያለሽ ከተማ ሆይ፥ በአንቺ ውስጥ የተገደሉት በሰይፍ የተገደሉ አይደሉም፥ በሰልፍም የሞቱ አይደሉም። 参见章节 |