Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 21:10 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

10 እናንተ በአውድማዬ ላይ የተወቃችሁ የአውድማዬ ልጆች ሆይ፥ ከእስራኤል አምላክ ከሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የሰማሁትን ነገርኳችሁ።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

10 በዐውድማ ላይ የተወቃህ ሕዝቤ ሆይ፤ ከሰራዊት ጌታ ከእግዚአብሔር፣ ከእስራኤል አምላክ፣ የሰማሁትን እነግርሃለሁ።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

10 ሕዝቤ እስራኤል ሆይ! ስንዴ በአውድማ ላይ እንደሚወቃ እናንተም ተወቅታችሁ ነበር፤ አሁን ግን የሠራዊት ጌታ፥ የእስራኤል አምላክ፥ የሰማሁትን የምሥራች ቃል ገለጥሁላችሁ።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

10 እና​ንተ የተ​ረ​ፋ​ች​ሁና መከራ የም​ት​ቀ​በሉ ሆይ፥ የእ​ስ​ራ​ኤል አም​ላክ የሠ​ራ​ዊት ጌታ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር የነ​ገ​ረ​ኝ​ንና የሰ​ማ​ሁ​ትን ስሙ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

10 እናንተ በአውድማዬ ላይ የተወቃችሁ የአውድማዬ ልጆች ሆይ፥ ከእስራኤል አምላክ ከሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር የሰማሁትን ነገርኋችሁ።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 21:10
13 交叉引用  

ሚክያስ ግን “ጌታ የሚገልጥልኝን ቃል ብቻ እንደምናገር በሕያው ጌታ ስም እምላለሁ!” ሲል መለሰለት።


ንጉሥ ኢዮአካዝ ከኀምሳ ፈረሰኞች፥ ከዐሥር ሠረገሎችና ከዐሥር ሺህ ወታደሮች በቀር ሌላ የተደራጀ የጦር ኃይል አልነበረውም፤ ይህም የሆነበት ምክንያት ሌላውን ሠራዊቱን የሶርያ ንጉሥ በአውድማ እንዳለ እብቅ ስለ ደመሰሰበት ነው።


እንጀራን ለመጋገር እህል ይፈጫል፤ ነገር ግን ለዘለዓለም አይፈጨውም፤ የሠረገላውን መንኰራኵርና ፈረሶቹን ምንም ቢያስኬድበት አያደቀውም።


የሚያልም ነቢይ ሕልምን ይናገር፤ ቃሌም ያለበት ቃሌን በእውነት ይናገር። ገለባ ከስንዴ ጋር ምን አለው? ይላል ጌታ።


የእስራኤል አምላክ የሠራዊት ጌታ እንዲህ ይላልና፦ “የባቢሎን ሴት ልጅ በመረገጥ ላይ እንዳለ ዐውድማ ነች፤ ጥቂት ቈይታ የመከር ጊዜ ይደርስባታል።”


ሰውዬውም እንዲህ አለኝ፦ “የሰው ልጅ ሆይ፥ በዓይንህ እይ፥ በጆሮህም ስማ፥ የማሳይህን ሁሉ ልብ ብለህ አስተውል፥ ይህን እንዳሳይህ ወደዚህ ተመርተሃልና የምታየውንም ሁሉ ለእስራኤል ቤት ንገር።”


አንበሳው አገሣ፤ የማይፈራ ማን ነው? ጌታ እግዚአብሔር ተናገረ፤ ትንቢት የማይናገር ማን ነው?”


የጽዮን ልጅ ሆይ ተነሺ አሂጂ፥ ቀንድሽን ብረት፥ ኮቴሽንም ናስ አደርጋለሁና፤ ብዙ ሕዝቦችን ታደቅቂአለሽ፤ እኔም ትርፋቸውን ለጌታ፥ ሀብታቸውንም ለምድር ሁሉ ጌታ አውለዋለሁ።


በቁጣ ምድርን ረገጥሃት፥ አሕዛብን በንዴት አሄድሃቸው።


መንሹ በእጁ ነው፤ አውድማውንም ያጠራል፤ ስንዴውን በጎተራ ይከተዋል፥ ገለባውን ግን በማይጠፋ እሳት ያቃጥለዋል።”


跟着我们:

广告


广告