Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 14:27 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

27 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ይህን አስቦአል፤ የሚያስጥለውስ ማን ነው? እጁም ተዘርግታለች፤ የሚመልሳትስ ማን ነው?

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

27 የሰራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ አስቧል፤ ማንስ ያግደዋል? እጁም ተዘርግቷል? ማንስ ይመልሰዋል?

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

27 የሠራዊት አምላክ ይህን ሁሉ ለማድረግ ወስኖአል፤ ይህ እንዳይሆን የሚያደርግ ማነው? ለመቅጣትም ክንዱን ዘርግቶአል፤ ተከላክሎ ሊያቆመው የሚችልስ ማን ነው?

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

27 ቅዱስ እግ​ዚ​አ​ብ​ሔር ይህን መክ​ሮ​አል፤ የእ​ግ​ዚ​አ​ብ​ሔ​ርን ምክር የሚ​መ​ልስ ማን ነው? የተ​ዘ​ረ​ጋች እጁ​ንስ የሚ​መ​ል​ሳት ማን ነው?

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

27 የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ይህን አስቦአል፥ የሚያስጥለውስ ማን ነው? አጁም ተዘርግታለች፥ የሚመልሳትስ ማን ነው?

参见章节 复制




ኢሳይያስ 14:27
22 交叉引用  

እርሱም እንዲህ አለ፦ “አቤቱ፥ የአባቶቻችን አምላክ ሆይ! በሰማይ ያለህ አምላክ አንተ አይደለህምን? የአሕዛብንስ መንግሥታት ሁሉ የምትገዛ አንተ አይደለህምን? ኃይልና ሥልጣን በእጅህ ነው፥ ሊቋቋምህም የሚችል የለም።


እርሱ ቢያልፍ፥ ቢዘጋም፥ ጉባኤንም ቢሰበስብ፥ የሚከለክለው ማን ነው?


እርሱ ግን የሚተካከለው የለውም፥ ማንስ ውሳኔውን ያስቀይረዋል? የወደደውንም ያደርጋል።


በውኑ ፍርዴን ታፈርሳለህን? አንተስ ጻድቅ ትሆን ዘንድ በእኔ ላይ ትፈርዳለህን?


“ሁሉንም ማድረግ እንድምትችል፥ ሐሳብህም ሊከለከል ከቶ እንደማይቻል አወቅሁ።


እነሆ፥ ፈጥኖ ቢነጥቅ የሚከለክለው ማን ነው? እርሱንስ፦ ምን ታደርጋለህ? የሚለው ማን ነው?”


የጌታ ምክር ግን ለዘለዓለም ይኖራል፥ የልቡም አሳብ ለልጅ ልጅ ነው።


በሰው ልብ ብዙ አሳብ አለ፥ የጌታ ምክር ግን እርሱ ይጸናል።


ያለ ጌታ የሚሠምር፥ ጥበብም የለም፥ ማስተዋልም የለም፥ ምክርም የለም።


የክብርን ሁሉ ትዕቢት ሊሽር፥ የምድርንም ክብር ሁሉ ሊያስንቅ የሠራዊት ጌታ ይህን ወስኗል።


እኔም አምላክ ነኝ፥ ከጥንት ጀምሮ እኔ ነኝ ከእጄም የሚያመልጥ የለም፤ እሠራለሁ፥ የሚከለክልስ ማን ነው?


ከምሥራቅ ነጣቂ ወፍን፥ ከሩቅም አገር ምክሬን የሚያደርገውን ሰው እጠራለሁ። ተናግሬአለሁ እፈጽምማለሁ፤ አስቤአለሁ አደርግማለሁ።


ተመካከሩ፤ ግን አይሳካም፤ ዕቅድ አውጡ፤ ሆኖም አይጸናም፤ እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ነውና።


ሕዝቡ ግን ወደ ቀጣቸው ፊታቸውን አልመለሱም፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርንም አልፈለጉም።


ስለዚህ ምድር ታለቅሳለች፥ በላይም ሰማይ ይጠቁራል፤ ተናግሬአለሁና፥ አስቤአለሁም፤ አልጸጸትም ከእርሱም አልመለስም።”


ከሰይፍም ያመለጡት ጥቂት ሰዎች ከግብጽ ምድር ወደ ይሁዳ ምድር ይመለሳሉ፤ በዚያም ለመቀመጥ ወደ ግብጽ ምድር የገቡት የይሁዳ ትሩፍ ሁሉ ከእኔ ወይም ከእነርሱ የማናችን ቃል እንደሚጸና በውኑ ያውቃሉ!


ስለዚህ ጌታ በኤዶምያስ ላይ የመከረባትን ምክር፥ በቴማንም በሚኖሩ ሰዎች ላይ ያሰባትን አሳብ ስሙ፤ በእውነት የመንጋው ትንንሾች እንኳ ይጐትቷቸዋል፤ በእውነት የማደሪያቸውም በረት በእነርሱ ላይ ይሣቀቃል።


የመሕሤያ ልጅ የኔርያ ልጅ ሠራያ የይሁዳ ንጉሥ ሴዴቅያስ በነገሠ በአራተኛው ዓመት ከእርሱ ጋር ወደ ባቢሎን በሄደ ጊዜ ነቢዩ ኤርምያስ ያዘዘው ቃል ይህ ነው። ሠራያም የሻለቃ መጋቢ ባሻ አዛዥ ነበረ።


የተራቆተ ዓለት አደርግሻለሁ፤ የመረብ ማስጫ ትሆኛለሽ፤ ዳግምም አትሠሪም፤ እኔ ጌታ ተናግሬአለሁና፥ ይላል ጌታ እግዚአብሔር።


እግዚአብሔርንም ለሚወዱት እንደ ዓላማውም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን።


እንግዲህ ስለ እነዚህ ነገሮች ምን እንላለን? እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ከሆነ ማን ይቃወመናል?


跟着我们:

广告


广告