Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ኢሳይያስ 10:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 ከእስረኞች ጋር ከመርበትበት፤ ከታረዱትም ጋር ከመጣል በቀር ምንም አይተርፋችሁም። ይህም ሁሉ ሆኖ፤ ቁጣው ገና አልበረደም። እጁም እንደ ተዘረጋ ነው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ከእስረኞች ጋራ ከመርበትበት፣ ከታረዱትም ጋራ ከመጣል በቀር ምንም አይተርፋችሁም። በዚህም ሁሉ እንኳ ቍጣው ገና አልበረደም፤ እጁም እንደ ተነሣ ነው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 ከመማረክና ከመገደል እንዴት ታመልጣላችሁ? ይህም ሁሉ ሆኖ የእግዚአብሔር ቊጣ ገና አልበረደም፤ ስለዚህ እናንተን ለመቅጣት እጁ እንደ ተሰነዘረ ነው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 በሐ​ሣር እን​ዳ​ት​ወ​ድቁ፥ ክብ​ራ​ች​ሁን ወዴት ትተ​ዉ​ታ​ላ​ችሁ? በዚ​ህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አል​ተ​መ​ለ​ሰ​ችም፤ ነገር ግን እጁ ገና ተዘ​ር​ግታ ትኖ​ራ​ለች።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ከእስረኞች በታች ያጐነብሳሉ፥ ከተገደሉትም በታች ይወድቃሉ። በዚህም ሁሉ እንኳ ቍጣው አልተመለሰችም፥ ነገር ግን እጁ ገና ተዘርግታ ትኖራለች።

参见章节 复制




ኢሳይያስ 10:4
19 交叉引用  

አንቺ ጩኸትና ፍጅት የሞላብሽ ከተማ፥ የፈንጠዚያ ከተማ ሆይ፥ በአንቺ ውስጥ የተገደሉት በሰይፍ የተገደሉ አይደሉምን፥ በሰልፍስ የሞቱ አይደሉም?


በጉድጓድ እንደሚከማቹ እስረኞች በአንድነት ይከማቻሉ፤ በግዞት ቤትም ውስጥ ተዘግተው ይኖራሉ፥ ከብዙ ቀንም በኋላ ይቀጣሉ።


ከእነርሱም የተገደሉት ይጣላሉ። ሬሳቸውም ይከረፋል፤ ተራሮችም በደማቸው ይርሳሉ።


የጌታ ቁጣ በሕዝቡ ላይ ነዶአል፤ እጁን አንሥቶ መቶአቸዋል፤ ተራሮች ራዱ፤ ሬሳዎችም በመንገድ ላይ እንደ ተጣለ ጥራጊ ሆኑ፤ ይህ ሁሉ ሆኖ ግን ቁጣው ገና አልተመለሰም፤ እጁም እንደ ተነሣ ነው።


ጌታም በሥጋ ለባሽ ሁሉ ላይ በእሳትና በሰይፉ ይፈርዳል፤ በጌታም ተወግተው የሞቱት ይበዛሉ።


ሶርያውያን ከምሥራቅ፤ ፍልስጥኤማውያን ከምዕራብ፤ አፋቸውን ከፍተው እስራኤልን ይቦጫጭቋታል። ይህም ሁሉ ሆኖ፤ ቁጣው ገና አልበረደም፤ እጁ እንደ ተዘረጋ ነው።


ሕዝቡ ግን ወደ ቀጣቸው ፊታቸውን አልመለሱም፤ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔርንም አልፈለጉም።


ስለዚህ ጌታ በጎበዛዝት ደስ አይሰኝም፤ አባት ለሌላቸውና ለመበለቶች አይራራም፤ ሁሉም ፈሪሀ እግዚአብሔር ያላደረበትና ክፉ አድራጊ ነው፤ የሁሉ አፍ አስጸያፊ ቃል ይናገራልና። ይህም ሁሉ ሆኖ፤ ቁጣው ገና አልበረደም፤ እጁም እንደ ተዘረጋ ነው።


እንግዲህ ርኩሰት እንደ እሳት ይቀጣጠላል፤ እሾህንና ኩርንችትን ይበላል፤ ጥቅጥቅ ያለውን ደን ያነዳል፤ ጢሱም ተትጐልጉሎ እንደ ዐምድ ይቆማል።


ምናሴ ኤፍሬምን፤ ኤፍሬም ምናሴን ይበላል፤ በይሁዳም ላይ በአንድነት ይነሣሉ፤ ይህም ሁሉ ሆኖ፤ ቁጣው ገና አልበረደም፤ እጁም እንደ ተዘረጋ ነው።


እነርሱም፦ ‘ወዴት እንውጣ?’ ቢሉህ፥ አንተ፦ ጌታ እንዲህ ይላል፦ ‘ለሞት የሆነ ወደ ሞት፥ ለሰይፍም የሆነ ወደ ሰይፍ፥ ለራብም የሆነ ወደ ራብ፥ ለምርኮም የሆነ ወደ ምርኮ’ ትላቸዋለህ።


እናንተንም የሚወጉዋችሁን የከለዳውያንን ሠራዊት ሁሉ ድል ብታደርጉ እንኳ ከእነርሱም መካከል የቆሰሉ ሰዎች ብቻ ቢቀሩ፥ እነርሱም ሁሉ ከየድንኳኖቻቸው ይነሣሉ ይህችንም ከተማ በእሳት ያቃጥላታል።’ ”


የጌታ ጽኑ ቁጣ ከእኛ ላይ አልተመለሰምና ማቅ ልበሱ፥ አልቅሱም ዋይም በሉ።”


ልጆቻቸውንም ቢያሳድጉ እንኳ አንድም ሰው ሳላስቀር ልጅ አልባ አደረጋቸዋለሁ፤ ከእነርሱም በራቅሁ ጊዜ ወዮላቸው!


ፊቴንም አጠቊርባችኋለሁ፥ በጠላቶቻችሁም ፊት ትሸነፋላችሁ፤ የሚጠሉአችሁም ይገዙአችኋል፤ ማንም ሳያሳድዳችሁ ትሸሻላችሁ።


እርሱ አንባቸው ካልሸጣቸው፥ ጌታም አሳልፎ ካልሰጣቸው፥ እንዴት አንዱ ሺህን ያሳድዳል? ሁለቱስ እንዴት ዐሥር ሺህ ያባርራሉ?


跟着我们:

广告


广告