Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 47:4 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

4 “በምድር ልንቀመጥ በእንግድነት መጣን፥ ራብ በከነዓን ምድር እጅግ ጸንቶአልና፥ የአገልጋዮችህ በጎች የሚሰማሩበት ስፍራ የለም፥ አሁንም አገልጋዮችህ በጌሤም ምድር እንድንቀመጥ እንለምንሃለን።” አሉት ፈርዖንን።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

4 ደግሞም፣ “በከነዓን ምድር ራቡ እጅግ የጸና በመሆኑ በጎችና ፍየሎች የሚሰማሩበት በማጣታቸው፣ ለጊዜው እዚህ ለመኖር መጥተናል፤ አሁንም ባሮችህ በጌሤም ምድር እንድንኖር እንድትፈቅድልን እንለምንሃለን” አሉት።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

4 በከነዓን ምድር ራብ እጅግ ከመበርታቱ የተነሣ ለእንስሶቻችን ግጦሽ ስላጣን ለጊዜው በዚህች አገር ለመኖር መጥተናል፤ ስለዚህ አገልጋዮችህ በጌሴም ምድር እንድንኖር ፍቀድልን።”

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

4 ፈር​ዖ​ን​ንም እን​ዲህ አሉት፥ “በም​ድር ልን​ቀ​መጥ በእ​ን​ግ​ድ​ነት መጣን፤ የአ​ገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ በጎች የሚ​ሰ​ማ​ሩ​በት ስፍራ የለ​ምና፤ ራብም በከ​ነ​ዓን ምድር እጅግ ጸን​ቶ​አ​ልና፤ አሁ​ንም አገ​ል​ጋ​ዮ​ችህ በጌ​ሤም ምድር እን​ቀ​መጥ።”

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

4 ፈርዖንንም እንዲህ አሉት፦ በምድር ልንቀመጥ በእንግድነት መጣን የባርያዎችህ በጎች የሚስማሩበት ስፍራ የለምና ራብ በከነዓን ምድር እጅግ ጸንቶቸልና አሁንም ባርያዎችህ በጌሤም ምድር እንድንቀመጥ እንለምንሃለን።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 47:4
11 交叉引用  

በምድርም ራብ ሆነ፥ አብራምም በዚያ በእንግድነት ይቀመጥ ዘንድ ወደ ግብጽ ወረደ፥ በምድር ራብ ጸንቶ ነበርና።


አብራምንም አለው፦ “ዘርህ ለእርሱ ባልሆነች ምድር ስደተኞች እንደሚሆኑ በእርግጥ እወቅ፥ ባርያዎች አድርገውም አራት መቶ ዓመት ያስጨንቋቸዋል።


ራቡ አሁንም በምድሪቱ ላይ እንደ ጸና ነበር፤


አንተና ልጆችህ የልጆችህም ልጆች፥ በጎችህና ላሞችህ ከብትህም ሁሉ፥ ከእኔም በቅርበት፥ በጌሤምም ምድር ትቀመጣለህ።


በግ ጠባቂ ሁሉ ለግብጽ ሰዎች ርኩስ ነውና፥ በጌሤም እንድትቀመጡ፦ ‘እኛ አገልጋዮችህ ከብላቴናነታችን ጀምረን እስከ አሁን ድረስ፥ እኛም አባቶቻችንም፥ እንስሳ አርቢዎች ነን’ በሉት።”


ፈርዖንም ዮሴፍን እንዲህ አለው፦ “አባትህና ወንድሞችህ መጥተውልሃል፥


እስራኤልም ወደ ግብጽ ገባ፥ ያዕቆብም በካም አገር ተቀመጠ።


ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፦ ወገኔ በዚያ እንግዳ ሆኖ ይቀመጥ ዘንድ አስቀድሞ ወደ ግብጽ ወረደ፥ አሦርም ያለ ምክንያት በደለው።


በግብጽና በከነዓንም አገር ሁሉ ራብና ብዙ ጭንቅ መጣ፤ አባቶቻችንም ምግብን አላገኙም።


እግዚአብሔርም ዘሩ በሌላ አገር መጻተኞች እንዲሆኑ አራት መቶ ዓመትም ባርያዎች እንዲያደርጉአቸው እንዲያስጨንቁአቸውም እንዲህ ተናገረ፤


አንተም በጌታ እግዚአብሔር ፊት እንዲህ ብለህ ትናገራለህ፥ ‘አባቴ ከቦታ ወደ ቦታ በመዞር የሚኖር ሶርያዊ ነበር፤ ከጥቂት ሰዎችም ጋር ወደ ግብጽ ወርዶ እዚያ ተቀመጠ። ከዚያም ታላቅ፥ ኀያልና ቁጥሩ የበዛ ሕዝብ ሆነ።


跟着我们:

广告


广告