Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 46:31 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

31 ዮሴፍም ወንድሞቹንና የአባቱን ቤተ ሰዎች እንዲህ አላቸው፦ “እኔ መጥቼ ለፈርዖን፦ ‘እንግዲህ በከነዓን ምድር የነበሩት ወንድሞቼና የአባቴ ቤት ሰዎች ወደ እኔ መጥተዋል፥

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

31 ከዚህ በኋላ ዮሴፍ ወንድሞቹንና የአባቱን ቤተ ሰዎች እንዲህ አላቸው፤ “ወደ ፈርዖን ወጥቼ አናግረዋለሁ፤ እንዲህም እለዋለሁ፣ ‘በከነዓን ምድር የሚኖሩት ወንድሞቼና የአባቴ ቤተ ሰዎች ወደ እኔ መጥተዋል።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

31 ከዚህ በኋላ ዮሴፍ ወንድሞቹንና የቀረውን የአባቱን ቤተሰብ እንዲህ አላቸው፤ “ወደ ፈርዖን ልሂድና ‘በከነዓን ምድር ይኖሩ የነበሩት ወንድሞቼና የቀሩትም የአባቴ ቤተሰቦች ወደ እኔ መጥተዋል፤

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

31 ዮሴ​ፍም ወን​ድ​ሞ​ቹን እን​ዲህ አላ​ቸው፥ “እኔ ሄጄ ለፈ​ር​ዖን እን​ዲህ ብዬ እነ​ግ​ረ​ዋ​ለሁ፦ በከ​ነ​ዓን ምድር የነ​በ​ሩት ወን​ድ​ሞ​ችና የአ​ባቴ ቤተ ሰዎች ወደ እኔ መጥ​ተ​ዋል፤

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

31 ዮሴፍም ወንድሞቹንና የአባቱን ቤተ ስዎች እንዲህ አላቸው፦ እኔ መጥቼ ለፈርዖን እንዲህ ብዬ እነግረዋለሁ፦ በከነዓን ምድር የነበሩት ወንድሞቼና የአባቴ ቤተ ሰዎች ወደ እኔ መጥተዋል፤

参见章节 复制




ዘፍጥረት 46:31
6 交叉引用  

እስራኤልም ዮሴፍን፥ “አንተ በሕይወት መኖርህን ፊትህን አይቼ አረጋግጫለሁና፥ አሁን ልሙት አለው።”


እነርሱም በግ የሚጠብቁ ሰዎች ናቸው፥ እንስሳ ያረቡ ነበርና፥ በጎቻቸውንና ላሞቻቸውን ያላቸውንም ሁሉ አመጡ፥’ ብዬ እነግረዋለሁ።


ሥራቸውም አንድ ስለ ነበረ በእነርሱ ዘንድ ተቀምጦ በአንድ ላይ ሠሩ፤ ሥራቸው ድንኳን መስፋት ነበረና።


የሚቀድሰውና በእርሱም የተቀደሱት ሁሉ መገኛቸው ከአንድ ነውና፤ ከዚህ የተነሣ ወንድሞች ብሎ ሲጠራቸው አያፍርም፤


跟着我们:

广告


广告