Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 41:54 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

54 ዮሴፍ አስቀድሞ እንደ ተናገረው የሰባቱ ዓመት የራብ ዘመን ጀመረ። ሌሎች አገሮች ሁሉ ሲራቡ፥ በመላው የግብጽ ምድር ግን ምግብ ነበር።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

54 ዮሴፍ አስቀድሞ እንደ ተናገረው የሰባቱ ዓመት የራብ ዘመን ጀመረ። ሌሎች አገሮች ሁሉ ሲራቡ፣ በመላው የግብጽ ምድር ግን ምግብ ነበር።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

54 ዮሴፍ አስቀድሞ እንደ ተናገረው፥ ሰባቱ የራብ ዓመቶች መግባት ጀመሩ፤ በሌሎች አገሮች ሁሉ ራብ ሆነ፤ ይሁን እንጂ በመላው የግብጽ ምድር በቂ ምግብ ነበር።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

54 ዮሴ​ፍም እንደ ተና​ገረ ሰባቱ የራብ ዓመት መም​ጣት ጀመረ። በየ​ሀ​ገ​ሩም ሁሉ ራብ ሆነ፤ በግ​ብፅ ምድር ሁሉ ግን እህል ነበረ።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

54 ዮሴፍም እንደ ተናገረ የሰባቱ ዓመት ራብ ጀመረ። በየአገሩም ሁሉ ራብ ሆነ በግብፅ ምድር ሁሉ ግን እህል ነበረ።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 41:54
13 交叉引用  

ከእነርሱም በኋላ ዐጥንታቸው የወጣ አስከፊ መልክ ያላቸው ሰባት ላሞች፥ ሰባት ዓመታት ናቸው፤ እንደዚሁም ፍሬ አልባ የሆኑትና በምሥራቅ ነፋስ ተመትተው የደረቁት ሰባት የእሸት ዛላዎች ሰባት የራብ ዓመታት ናቸው።


ከዚህ በኋላ ግን በተከታታይ ሰባት የራብ ዓመታት ይሆናሉ። የራቡ ዘመን አገሪቱን እጅግ ስለሚጐዳት፥ በግብጽ የነበረው ያለፈው የጥጋብ ዘመን ሁሉ ጨርሶ አይታወስም።


በግብጽ ምድር የነበረው ሰባቱ የጥጋብ ዘመን ዐለፈና


በግብጽ እህል መኖሩን ሰምቻለሁ፤ ስለዚህ ከመሞት መሰንበት ይሻላልና ወደዚያው ወርዳችሁ እህል ሸምቱልን” አላቸው።


ራቡ አሁንም በምድሪቱ ላይ እንደ ጸና ነበር፤


በዚያም፥ የራቡ ዘመን ገና አምስት ዓመት ቀርቶአልና፥ አንተና የቤትህ ሰዎች የአንተ የሆነው ሁሉ እንዳትቸገሩ እመግብሃለሁ።’


ራብም እጅግ ጸንቶአልና፥ በምድር ሁሉ እህል አልነበረም፥ ከራብም የተነሣ የግብጽ ምድርና የከነዓን ምድር ተጎዳ።


ልጇን ከሞት ያስነሣላትን፥ በሱነም ትኖር የነበረችውን ሴት እነሆ፥ ኤልሳዕ አስቀድሞ እንዲህ ሲል ነግሮአት ነበር፥ “እግዚአብሔር እስከ ሰባት ዓመት የሚቆይ ራብ በዚህች ምድር ላይ ልኮአል፤ ከቤተሰብሽ ጋር በሕይወት ለመትረፍ ከዚህ ተነሥተሽ ወደ ሌላ ስፍራ ሂጂ።”


በምድር ላይ ራብን ጠራ፥ የእህልን ኃይል ሁሉ ሰበረ።


በግብጽና በከነዓንም አገር ሁሉ ራብና ብዙ ጭንቅ መጣ፤ አባቶቻችንም ምግብን አላገኙም።


跟着我们:

广告


广告