Biblia Todo Logo
在线圣经

- 广告 -




ዘፍጥረት 38:14 - መጽሐፍ ቅዱስ - (ካቶሊካዊ እትም - ኤማሁስ)

14 የመበለትነት ልብሷን አውልቃ፥ ማንነቷ እንዳይታወቅ ፊቷን በሻሽ ተከናንባ ወደ ተምና በሚወስደው መንገድ ዳር ባለች ኤናይም በተባለች ከተማ መግቢያ ላይ ተቀመጠች፤ ይህን ያደረገችው፥ ሴሎም ለአካለ መጠን ቢደርስም፥ እርሷን እንዲያገባ አባቱ አለመፈለጉን ስላወቀች ነው።

参见章节 复制

አዲሱ መደበኛ ትርጒም

14 የመበለትነት ልብሷን አውልቃ፣ ማንነቷ እንዳይታወቅ ፊቷን በሻሽ ተከናንባ ወደ ተምና በሚወስደው መንገድ ዳር ባለች ኤናይም በተባለች ከተማ መግቢያ ላይ ተቀመጠች፤ ይህን ያደረገችው፣ ሴሎም ለአካለ መጠን ቢደርስም፣ እርሷን እንዲያገባ አባቱ አለመፈለጉን ስላወቀች ነው።

参见章节 复制

አማርኛ አዲሱ መደበኛ ትርጉም

14 ስለዚህ ትዕማር የመበለትነት ልብሷን ለውጣ ፊቷን በሻሽ ሸፈነች፤ ወደ ቲምና በሚወስደው መንገድ ዳር በዔናይም ደጅ ተቀመጠች፤ ይህንንም ያደረገችው ሴላ አድጎ ሳለ ለእርሱ በሚስትነት እንድትሰጥ አለመፈቀዱን ስለ ተረዳች ነው።

参见章节 复制

የአማርኛ መጽሐፍ ቅዱስ (ሰማንያ አሃዱ)

14 እር​ስ​ዋም የመ​በ​ለ​ት​ነ​ቷን ልብስ አወ​ለ​ቀች፤ መጐ​ና​ጸ​ፊ​ያ​ዋ​ንም ለበ​ሰች፤ ተሸ​ፈ​ነ​ችም፤ ወደ ተም​ናም በሚ​ወ​ስ​ደው መን​ገድ ዳር በኤ​ና​ይም ደጅ ተቀ​መ​ጠች፤ ሴሎም እንደ አደገ፥ ሚስ​ትም ትሆ​ነው ዘንድ እር​ስ​ዋን ሊሰ​ጠው እን​ዳ​ል​ፈ​ለገ አይ​ታ​ለ​ችና።

参见章节 复制

መጽሐፍ ቅዱስ (የብሉይና የሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት)

14 እርስዋም የመበለትነትዋን ልብስ አወለቀች፥ መጎናጸፊያዋንም ወሰደች ተሸፈነችም ወደ ተምናም በሚወስደው መንገድ ዳር በኤናይም ደጅ ተቀመጠች ሴሌም እንደ አደገ ሚስትም እንዳልሆነችው አይታለችና።

参见章节 复制




ዘፍጥረት 38:14
9 交叉引用  

ሎሌውንም፦ “ሊገናኘን በሜዳ የሚመጣ ይህ ሰው ማን ነው?” አለችው።


ፊቷ በሻሽ ተሸፋፍኖ ሲያያት፥ ይሁዳ ዝሙት ዐዳሪ መሰለችው።


ከዚያም ወደ መኖሪያዋ ተመልሳ፥ ሻሽዋን አውልቃ እንደ ወትሮዋ የመበለት ልብሷን ለበሰች።


ይሁዳም ዕቃዎቹን ዐውቆ፥ “ልጄ ሴሎም እንዲያገባት ባለማድረጌ፥ እርሷ ከእኔ ይልቅ ትክክል ናት” አለ። ከዚያም በኋላ ከእርሷ ጋር አልተኛም።


እነሆ፥ ሴት ተገናኘችው የአምንዝራ ሴት ልብስ የለበሰች፥ ነፍሳትን ለማጥመድ የተዘጋጀች።


አንድ ጊዜ በጎዳና፥ አንድ ጊዜ በአደባባይ፥ በማዕዘኑም ሁሉ ታደባለች።


ወደ ተራቈቱ ኮረብቶች አይኖችሽን አንሺ፥ ተመልከቺም፤ ያልተጋደምሽበት ስፍራ ወዴት አለ? ልክ በምድረ በዳ እንደሚቀመጥ አረባዊ አንቺ በመንገድ ላይ ተቀምጠሽ ትጠብቂያቸዋለሽ፤ በግልሙትናሽና በኃጢአትሽ ምድሪቱን አረከስሽ።


በየመንገዱ ራስ ሁሉ ላይ ከፍ ያለውን ቦታሽን ሠራሽ፥ ውበትሽንም አረከስሽ፥ ለአላፊ አግዳሚው ሁሉ እግርሽን ከፈትሽ፥ አመንዝራነትሽንም አበዛሽ።


跟着我们:

广告


广告